
የጤና ሴክተር የጋራ የምክክር (ጂ ኤስ ሲ) መድረክ በሳጃ ከተማ ማካሄዱን የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ ገልጿል።
በበጀት አመቱ በመጀመሪያው ሩብ አመት በጤናው ሴክተር ትኩረት ተሰጥቶ የተከናወኑ ተግባራት እና በቀጣይ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ውጤቶችን ለማስመዝገብ ባለድርሻ አካላት ተቀራርበው ሊሰሩ እንደሚገባ ተገልጿል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ለጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በቁርጠኝነት ለመደገፍ ሁሉም ባለድሻ አካል የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
የማህበረሰቡን የጤና ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት አመራሩና ባለሙያው በቅንጅት የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ፋይዳው የጎላ እንደሆነም ተናግረዋል።
በየደረጃው በአፈጻጸም ወቅት የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች ለመቅረፍ የጤናው ሴክተር አመራሮች በየደረጃው ካሉ የዞንና የልዩ ወረዳ የፊት አመራሮች ጋር በቅርበት ተግባራትን ሊያከናውኑ እንደሚገባም አቶ ሳሙኤል አክለው ገልጸዋል።
የእናቶች እና ህጻናት ጤናን በማሻሻል ረገድ የሚስተዋሉ ጉድለቶችን ማረም ይገባል ያሉት ኃላፊው የማዐጤማ ኦዲት በአግባቡ ማድረግ ፣ የመረጃ ልውውጥ እና ጥራት፣ የማህበረሰብ መድሃኒት ቤትን ማስፋፋት ፣ የህገ ወጥ የመድኃኒት ዝውውርን ማስቆም፣ የኮምፕሬሄንሲቭ እና የጤና ጣቢያ ተቋማት ግንባታን ማጠናከር እና መሰል ስራዎችን ለማሻሻል ተቀራርቦ እና ተቀናጅቶ ተግባራትን ለማሳለጥ ሁሉም ባለድሻ አካል ቁርጠኛ ሊሆን አንደሚገባ ተናግረዋል
የቢሮው ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ በበኩላቸው የጤናውን ሴክተር በአግባቡ ለማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክተውን የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም በማጠናከር ፍትሀዊና ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ አመላክተዋል።
በክልሉ የተከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎችን በመቆጣጠር፣ እና የቅድመ ትንበያ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ያሉት አቶ አሸናፊ የማህበረሰቡን ተሳትፎ በማጎት በአፈጻጸም ወቅት ለሚያጋጥሙ ተግዳሮቶች የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ ይገባል ብለዋል።
የወባ በሽታን በመቀነስ ረገድ አበረታች መኖራቸውንና ችግሩን ለመቆጣጠር የሚደረጉ ርብርቦች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የግብዓት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት የበኩላቸው ድርሻ ሊወጡ ይገባል ያሉት ምክትል ኃላፊው በመጀመሪያ ሩብ አመት አፈፃፀም ጠንካራ የነበሩ ጉዳዮችን በማጠናከር በጉድለት የተለዩ ጉዳዮችን ለማረም በልዩ ትኩረት መፈጸም እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ከፍተኛ አመራሩን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የወባ ወረርሽኝን ለመግታት እያደረጉ ያለውን ርብርብ አጠናክሮ በማስቀጠል በሽታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመቆጣጠር እንደሚቻል ተመላክቷል።
የማኔጅመንት አካላት በበኩላቸው ወደ ታች የሚወርዱ የጤና ግብአቶችና መገልገያ መሳሪያዎች እንዲሁም መድሃኒቶችን በአግባቡ ስራ ላይ ለማዋል የክትትል ስራዎች አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስረድተዋል ።
የውይይቱ ተሳታፊዎች እንደተናገሩት ቢሮው በጥናት የተደገፉ ጥናት እና ምርምር ማድረጉ አበረታች መሆኑን ጠቅሰው ቀጣይ ጥናቱ በተግባር መሬት ወርዶ ተግባራዊ መሆን ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
የማ/ ኢት/ክ/መ/ ጤና ቢሮ