በመሀሉ ዘመን ወጥመድ ውስጥ እንዳንቀር ትጋትና ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው-ም/ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ

  • Post last modified:May 8, 2025

ሚያዝያ 30/2017ዓ.ም በማህበራዊ ክላስተር “የመሀሉ ዘመን” በሚል መሪ ሀሳብ ለአመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በወራቤ ከተማ እየተሰጠ ነው።

ስልጠናውን የክልሉ ም/ ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ አስጀምረውታል።

ም/ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አንተነህ ፈቃዱ በዚህ ወቅት እንዳሉት በመሀሉ ዘመን ወጥመድ ውስጥ እንዳንቀር ትጋትና ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው።

በተለይም ብልሹ አሠራርን በማስወገድ፣ አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻልና በሁሉም መስክ ምርታማነትን ማሳደግ ላይ ርብርብ በማድረግ ከመሀል ዘመን ወጥመድ መውጣት ይገባል ብለዋል።

የስልጠናው ዋና ዓላማ የመሀሉ ዘመን ወጥመድ መሻገር በሚል እሳቤ የሚያጋጥሙ ፈተናዎችን መሻገር የሚያስችል አቅም መፍጠር መሆኑንም ገልጸዋል።

በአመራርና በአባሉ የጋራ መግባባት በመፍጠር መልካም ልምዶችን ማስቀጠል እና ውስንነቶችን ማረም የሚያስችል ስልጠና መሆኑንም አመላክተዋል ።

የስልጠናውን ሰነድ የማህበራዊ ክላስተር የብልጽግና ቤተሰብ ሰብሳቢና የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ቀርቦ በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።

በቀጣይም ስልጠናው በየደረጃው ለአባላት እና ለመንግስት ሰራተኞች እንደሚሰጥ ተገልጿል።