በመድሃኒት እና የህክምና መሳሪያ አቅርቦት ማሻሻል ላይ የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠል በየደረጃው ያለ አመራር ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ገለጹ ፡፡

  • Post last modified:July 8, 2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የመድኃኒት እና ህክምና መሳሪያዎች ዳይሬክቶሬት የ2017 በጀት ዓመት ተግባራት አፈፃፀም ግምገማ ተካሄደ ፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በአፈጻጸም መድረኩ ላይ እንዳሉት በበጀት ዓመቱ የመድሃኒት እና የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ችግር ለመፍታት በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል ፡፡

የመድሃኒት አቅርቦት ችግርን ለመፍታት ህብረተሰቡን ፣ባለሀብቱን አጋር አካላትን በማስተባበር በርካታ የማህበረሰብ መድሀኒት ቤቶች መገንባት መቻሉን የገለጹ ሲሆን በጤና የህክም መሳሪያዎች እና ቁናቁሳ ማሟላት ስራመሰራቱንም አስታውቀዋል ፡፡

የህክምና ግብዓት አቅርቦትን ለማሻሻል ከኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ እና ከሌሎች አካላት ጋር ያለው ቅንጅት ጥሩ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

የዘርፉን የግብዓት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በበጀት አመቱ የመድሃኒት እና የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ለውጥ እንዲመጣ ያስቻሉ የማህበረሰብ መድሃኒት ቤት ማስፋፋት እና የውስጥ አቅምን በመጠቀም በቀጣይም በሁሉም አካባቢ ማስፋት ይገባል ብለዋል ፡፡

ለዚህም በየደረጃው ያለ አመራር በቁርጠኝነት መስራት አለበት ብለዋል ፡፡

ከኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ጋር አስገዳጅ የመድሃኒት ግዢ ውል ስርዓት እንደሚጀመር ገልጸው ውጤታማ እንዲሆን በየደረጃው ያለው አመራር ለመድሀኒት ግዢ የሚውል በጀት ማስያዝ ቁርጠኝነት በየደረጃው ካለ አመራር ቁርጠኝነት እንደሚፈልግ አሳስበዋል ፡፡

የቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የህክምና አገልግሎቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብቴ ገብረ ሚካኤል በበኩላቸው የዘርፉን ችግሮች ለመፍታት በተሰራው ስራ ከፍተኛ ለውጥ ቢመጣም የህክምና ግብዓቶች አያያዝ እና አጠቃቀም ላይ መሰረታዊ ለውጥ መምጣት እንደሚገባ ገልጸዋል ፡፡

በቢኒያም ገዙ