
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እንዳሻው ጣሰው በክልሉ በቀዳማይ የልጅነት ልማት ፕሮግራም ልማት ማስጀመሪያ ላይ ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ከፕሮግራሙ አስተባባሪዎች ጋር ነው በጽ/ቤታቸው የተወያዩት ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ቀዳማይ የልጅነት ልማት ፕሮግራም በህጻናት ሁለንተናዊ እድገት፣ጤና እና ትምህርት ላይ የላቀ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።
በክልሉ ፕሮግራሙን ተግባራዊ ለማድረግ የክልሉ መንግስት በትኩረት ይሰራል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ የአዲስ አበባን የቀዳማይ የልጅነት ልማት ፕሮግራም ተሞክሮ በመውሰድ ከክልሉ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዛመድ መስራት አስፈላጊ ስለመሆኑም አብራርተዋል።
በቀዳማይ የልጅነት ልማት ፕሮግራም ላይ በማተኮር መስራት የሀገራችንን የትውልድ እጣ ፈንታ ለመወሰን እንደሚያስችልም ጠቁመዋል።
በመርሐ ግብሩ በቀዳማይ የልጅነት ፕሮግራም አተገባበር ላይ ያተኮረ የመወያያ ጽሁፍ ቀርቧል።
ለህጻናት ምቹ የመማሪያ እና የማቆያ ማዕከላት በማዘጋጀት የወደፊት እድገታቸውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባም ተመላክቷል።
ለማ/ክ/መ/ኮ/ጉ/ዘገባ
የማ/ኢት/ክ/መ/ ጤና ቢሮ