
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ነው የንቅናቄ መድረኩን በቡታጅራ ከተማ እያካሄደ ያለው።የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ መድረኩን ባስጀመሩበት ጊዜ እንዳሉት ዘርፈ ብዙ ማህበራዊ ብልጽግና ሊያረጋግጡ ከሚችሉ ቁልፍ ተግባራቶች ዋናው የጤና ሥርዓት ማሻሻል ነው።በዚህም በ2017 በጀት ዓመት የጤና ሥርዓት ሊያሻሽሉ የሚችሉ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል አቶ ሳሙኤል።ላለፉት ዓመታት ተቀዛቅዞ የነበረው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ጥናት በማድረግ ክልል አቀፍ ንቅናቄ ተደርጎ ወደ ሥራ መገባቱን አስታውሰዋል።የጤና ባለሙያዎች ትኩረት ሰጥተው መሥራት ያለባቸው በበሽታ መከላከል ዘርፍ ላይ በተደራሽነትና በጥራት እንዲሆን ኃላፊው አሳስበዋል።የህብረተሰቡን ጤና ተደራሽነት ለማሳደግ በበጀት ዓመቱ 7 አጠቃላይ ጤና ኬላ ለመገንባት ታቅዶ ወደ 17 ማሳደግ ተችሏል ነው ያሉት አቶ ሳሙኤል።የጤና ተቋማት አገልገሎት አሰጣጥ ለማሻሻል ስብጥሩን የጠበቀ የሰው ኃይል ለመሙላት በትኩረት ተሰርቷል ብለዋል።በመድረኩ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌን ጨምሮ የቢሮው ምክትል ኃላፊዎ፣ የጤና ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች፣ ከክልሉ ከሁሉም ጤና መዋቅሮች የተውጣጡ የጤና ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
አብርሃም ሙጎሮ
ለተጨማሪ መረጃ telegram https://t.me/centralethiopiarhb