በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የ2017 የማህበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድህን አጠቃላይ አፈጻጸም ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የክልሉ ወረዳ አስተዳደር እና ጤና ጽ/ቤቶች እውቅናና ሽልማት ተበረከተላቸው ፡፡

  • Post last modified:January 22, 2026

የሳንኩራ ወረዳ ፣አቶቴ ኡሎ ወረዳ እና የዌራ ዲጆ ወረዳ አስተዳደሮች እና ጤና ጽ/ቤቶች በቅደም ተከተላቸው ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ እውቅናና ሽልማት ተቀብለዋል ፡፡

እውቅና እና ሽልማቱን የወረዳዎቹ አስተዳዳሪዎች እና ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች ከጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶክተር ደረጀ ዱጉማ እጅ ተቀብለዋል ፡፡

ክልላዊ የ2017 የማህበረሰብ ዐቀፍ ጤና መድህን አፈጻጸም እና የ2018 ንቅናቄ መድረክ በሆሳዕና አዲሱ ርዕሰ መስተዳድር አዳራሽ በድምቀት ተካሂዷል ፡፡