በበጀት ዓመቱ በክልሉ ጥራቱን የጠበቀ የመድሀኒት እና የህክምና መሳሪያዎችን ተደራሽ ለማድረግ የተሰራው ስራ ውጤታማ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ገለፀ ፡፡

  • Post last modified:July 8, 2025

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የመድኃኒት እና ህክምና መሳሪያዎች ዳይሬክቶሬት የ2017 በጀት ዓመት ተግባራት አፈፃፀም ዓመታዊ የምክክር መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።

የእንኳን ደህና መጣችሁ የስልጤ ዞን የጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሸምሱ ሀይረዲን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር መድረኩን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት በዞኑ የህብረተሰቡን የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት እና የመድሀኒት አቅርቦት ችግርን በዘላቂነት ለመቅረፍ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

የአፈጻጸም መድረኩን በንግግር የከፈተቱት የጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊና የህክምና አገልግሎቶች ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሀብቴ ገ/ሚካኤል እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ ጥራቱን የጠበቀ አስተማማኝ የመድኃኒት እና የህክምና መሳሪያዎችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ መሰራቱን ገልፀዋል

ዜጎች አማራጭ የመድኃኒት አቅርቦትን በየአካባቢው እንዲያኙ በርካታ የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ተደራሽ እየተደረገ ይገኛል ያሉት አቶ ሀብቴ ይህ መደረጉ ህብረተሰቡ ጥራቱ የጠበቀ እና ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ መድኃኒት ለማቅረብ እያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

ከመንግስት የሚመጡ መድሀኒቶች ጥራታቸዉና የፈዋሽነት ደረጃቸው የተረጋገጠ ስለመሆኑ ያነሱት ም/ሀላፊዉ በእጃችን ያለዉን መድሀኒት ከብክነት በመጠበቅ በፍትሀዊነት በአግባቡ መጠቀምና ማስተዳደር እንደሚገባ አስረድተዋል

በ2017 በጀት ዓመት ማህብረተሰቡ በየአከባቢዉ በርካታ መድሀኒት ቤትን ከመገንባት ባለፈ የህክምና መሳሪያዎችን እና የመድሀኒት ግዢን በመፈፀም ለጤና መዋቅሩ ከፍተኛ አቅም መፍጠር መቻሉን የጠቆሙት አቶ ሀብቴ ይህን ስርዓት ዘላቂ በሆነ መልኩ በማጠናከር ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል ፡፡

የቢሮዉ የመድኃኒትና ህክምና መሳሪያዎች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳርጊቾ አህመድ የበጀት ዓመቱን ሪፓርት እያቀረቡ ይገኛሉ

በመድረኩ የቢሮዉ ምክትል ሀላፊዎችና የማኔጅመንት አባላት፣የኢት/ያ መድሀኒት አቅራቢ ድርጅት የደቡብ ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ ዘመን ለገሰ ፣ የዞን፣የልዩ ወረዳ፣የወረዳና ከተማ አስተዳደር የጤና ሀላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በሸምሲያ አደም