
በምስራቅ ጉራጌ ዞን የቡታጅራ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የተቀናጀ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባትና የጤና ዘመቻ መርሃ ግብር በከተማዋ በሁሉም አካባቢዎች አስጀመሯል።ዘመቻው ከግንቦት 6 እስከ 15/2017 የሚካሄደው ክትባት ከ6 እስከ 59 ወር ዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ህፃናት ብቻ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ዶ/ር ስናፍቅሽ አየለ በዘመቻው የሚሰጡ አገልግሎቶችን አቀናጅቶ ብዙ ህፃናትን መከተብ በሚያስችል መልኩ ማሳካት ይገባል።ከተማ ማስፋፊያ እና ጥግግት ያለበት መሀል ከተማ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ክትባቱን መስጠት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።የቡታጅራ ከተማ ጤና ተቋም በክትባት ዘመቻ አፈፃፀም ላይ የተሻለ ስራ እየሰራ የሚገኝ መሆኑንም ዶ/ር ስናፍቅሽ ጠቁመዋል።የጤና ጽ/ቤቱ ኃላፊ ተወካይ አቶ አህመድ መሀመድ የህፃናትን በሽታ መከላከል አቅም ከፍ የሚያደርግ ክትባት መሆኑን ተናግረዋል።የህፃናትን በሽታ የመከላከል አቅም መሰረት ያደረገ በሀገር አቀፍ ደረጃ ጥናት በማድረግ ተጨማሪ እንደሚያስፈልግ የተረጋገጠና ከ6 እስከ 59 ወር የእድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ የሚሰጥ ነው።ለአገልግሎቱ መሳካት ማህበረሰቡም አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግ አቶ አህመድ መሀመድ ጠይቀዋል።