በክልሉ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት በተሰሩ ሞዴል ስራዎች ላይ የፌደራል እና የተለያየ ክልል ልዑካን በተገኙበት የልምድ ልውውጥ ተካሄደ ፡፡

  • Post last modified:July 2, 2025

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ በማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት በተሰሩ ሞዴል ስራዎች ላይ የፌደራል እና የአራት ክልል ልዑካን በተገኙበት የልምድ ልውውጥ ተካሄደ ፡፡

በልምድ ልውውጡ ላይ ከፌደራል ጤና መድህን ኤጀንሲ፣ ከሲዳማ ክልል ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ከኦሮሚያ ክልል እና ከአማራ ክልል የተወጣጡ ልዑካን ቡድን በሀላባ ዞን የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን የዞን ከፍ ያለ ቋት ሞዴል ተግባር ላይ በሀላባ ዞን የልምድ ልዉዉጥ አድርገዋል ፡፡

ለዚህ ሞዴል አፈጻጸም የአመራር ድጋፍ እና ቁርጠኝነት ወሳኝ እንደነበር ፣ የማአጤመ ቦርድ ውይይት ላይ ውሳኔ ሰጪነት እያደገ መምጣቱ ለውጤቱ ጉልህ ሚና እንደነበረው የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል እና የህክምና አገልግሎቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብቴ ገብረ ሚካኤል ገልጸዋል ፡፡

በክልሉ በሶስት ዞኖች ከፍ ያለ ዞናል ቋት ወደ መሉ ትግበራ የገቡት ሀላባ የም እና ምስራቅ ጉራጌ ዞኖች ሲሆኑ ከምባታ ዞን በቅርቡ ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባ አስታውቀዋል ፡፡

የሀላባ ዞን በባለፉት አመታት በክልልም በፌደራልም በማአጤመ ላይ በሰራው ስራ ተሸላሚ ዞን መሆኑ ለዚህ ልምድ ልውውጥ መመረጡ አንስተዋል ፡፡

በቀጣይ ሁሉንም ዞኖች ከፍ ያለ ዞናል ቋት ስርዓት ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ መሆኑን አቶ ሀብቴ ገልጸዋል ፡፡

ዞናል ቋት በተመሰረተባቸው ዞኖች
የጤና አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል ፣ የመድሀኒት አቅርቦት እጥረት መፍታት ፣ ፣ የአባላት ምጣኔ እድገት መምጣቱን የገለጹት ኃላፊው ሃብትን በአንድ ቋት ማስተዳደር በመቻሉ የጤና ተቋማት የሀብት ችግር በማስወገድ አገልግሎት መቆራረጥ ችግር መፈታቱን ገልጸዋል ፡፡

የሀላባ ዞን ም/አስተዳደር እና የግብርና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሀጂ ኑርዬ እንኳን በደህና መጣችሁ ያሉ ስሆን በዞኑ በህዝብ ተሳትፎ የተለያዩ የጤና ተቋማት መገንባታቸውን ገልፀው ብልጽግና መረጋገጥ የሚቻለው ጤናው የተጠበቀውን ማህበረሰብ ስኖር ያሉት አቶ ሃጂ እንደ ዞኑ በጤናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል ።

የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ ዶ/ር ሸምሱ ረሺድ እንኳን በደህና መጣችሁ ያሉ ስሆን በዞኑ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ከሚገኘው ነገር አንዱ ጤና መሆኑ ገልጸው የሀላባ ቁሊቶ አጠቀላይ ሆስፒታል በህዝብ ተሳትፎ መገንባቱን በተጨማሪም በህዝቡ 6ጤና ጣቢያ ተገንብቶ ለአገልግሎት መብቃቱን ተናግረዋል ።

ብዙ ብሄር ብሄረሰቦች ተቻችለው የሚኖሩበትን እና ብዙም የመንግስት እጅ ሳይጠብቁ ህዝቡ በራሱ የራሱን ልማት በአንድነት ወደ ለሚሰራው ልማት ወዳዱ ወደ ሀላባ ህዝብ እንኳን በሰላም መጣችሁ ያሉት የሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከንቲባ አቶ ገመዳ መሀመድ የዛሬው ልምድ ልዉዉጥ እናንተም ከኛ ብዙ ልምድ አከብታችሁ የምትሄድበት እኛም ከናንተ ልምድ የምንወስድበት እንድሆን እመኛለሁ ብሏል።

በዚህም ልዑካን ቡድኑ የጋራ ትውውቅ በማድረግ በሀላባ ዞን አጠቀላይ ሆስፒታል ፣በሀላባ ጤና ጣቢያ እና በቁሊቶ ከተማ በዛላ ቀበሌ መሀል አረደ ቀጠና በመገኘት የተሰሩ ስራዎችን ተዟዙረው በመመልከት ልምድ ልዉዉጥ አድርገዋል ፡፡