በክልሉ የመድኃኒት ቁጥጥር ስራን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የተቀመጠውን ስታንዳር በተገቢዉ መተግበር እንደሚገባ ተጠቆመ

  • Post last modified:July 4, 2025

የማዕ/ ኢት/ ክልል ጤና ቢሮ የጤናና ጤና ነክ አገልግሎትቶች እና ግብአቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት የአፈፃፀም ግምገማ የማጠቃለያ መድረክ ተካሂዷል

የጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊና የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፋሲካ አለሙ በፕሮግራሙ ማጠቃለያ ላይ እንደተናገሩት በክልሉ የመድኃኒት ቁጥጥር ስራን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ የተቀመጠውን ስታንዳር በተገቢዉ መተግበር እንደሚገባ ጠቁመዋል ።

አቶ ፋሳካ አክለዉም ዘርፉን ይበልጥ ዉጤታማ ለማድረግ ዉስጣዊ ቅንጅትን በጋራ በማጎልበት የዜጎችን ጤና ሊጎዱ የሚችሉ ማንኛውም ህገ ወጥ ተግባርን መከላከል ይገባል ብለዋል

የመረጃ አያያዝ ስርዓታችንን ማጠናከር ይገባል ያሉት ም/ሀላፊዉ ለጤና ተቋማትም ሆነ ጤና ነክ ተቋማት የሙያ ፍቃድ ከመሰጠቱ በፊት መረጃን በተገቢው በማደራጀት የብቃት ደረጃቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል።

በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን አቶ ፋሲካ ሲያብራሩ ጠንካራ የሆነ የቁጥጥር መዋቅር መፍጠር ፣ ያለንን በጀት አብቃቅተንና ተደጋግፈን መስራት እንዲሁም ለቁጥጥር ስራዉ እንዲመች ተሽከርካሪ ማመቻቸት እንደሚገባ አስረድተዋል

ጠንካራ እና ዉጤታማ ስራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆን ይገባል ያሉት አቶ ፋሲካ ከሙስና ኒኪኪ ነፃ የሆነ የቁጥጥር ስራ ለመስራትና ጠንካራ ተቋም ለመፍጠር በጋራ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

የዉይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው መድረኩ አስተማሪና ስኬታማ እንደነበር ጠቅሰዉ የቁጥጥር ዘርፋን ለማጠናከር በክልሉ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በምርጥ ተሞክሮነት ወደ ታችኛዉ መዋቅር በማስፋት ዘርፉን ዉጤታማ ማድረግ ይገባል ብለዋል

መድረኩ የተሳካና ለቀጣይ ተግባራት ተሞክሮና ግብአት የተገኘበት ስለመሆኑም በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ተገልጿል ።

በመጨረሻም በ2017 በጀት ዓመት የላቀ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ዞኖች የማበረታቻ እና የእዉቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ።

በሸምሲያ አደም