በክልሉ የሚገኙ የጤና ተቋማቶችን

የፌደራል እና የክልል የስራ ኃላፊዎች
በክልሉ በሃዲያ ዞን በሆሳዕና ከተማ የሚገኙ የጤና ተቋማትን በመዘዋወር ጉብኝት አድርገዋል ፡፡
የስራ ኃላፊዎቹ የክልሉ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላብራቶሪ ሆሳዕና ቅርንጫፍ ፣ የንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮንፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፣ የሆሳዕና ጤና ሳይንስ ኮሌጅን በመዘዋወር ጉብኝት አድርገዋል ፡፡
በመጨረሻም የስራ ኃላፊዎቹ የሃዲያ ዞን ጤና መምሪያ የህብረተሰብ ጤና የድንገተኛ አደጋ ምላሽ መስጫ ክፍልን ምልከታ ተደርጓል ፡፡
የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የላብራቶሪ አገልግሎት ኃላፊ ዶ/ር ሳሮ አብደላ የጉብኝቱ ዓላማ በማዕከላዊ የኢትዮጵያ ክልል የላብራቶሪ አገልግሎት አሰጣጥ ያለበትን ሁኔታ በማየት በቀጣይ አብሮ ለመስራት የሚያስችል ውይይት ማድረግ ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን አመላክተዋል።
ለህብረተሰብ ተደራሽ የሆነና ጥራቱን የጠበቀ የላብራቶሪ አገልግሎት በክልሉ ተደራሽ ለማድረግ ከተቋሟት ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ዶ/ር ሳሮ አክለዋል።
በዛሬው ዕለት ተዛዋውረው ምልከታ ሲያደርጉ ጥሩ የሆነ ጅምር መኖሩን መመልከታቸውን የተናገሩት ዶ/ር ሳሮ ደረጃውን የጠበቀ የላብራቶሪ አገልግሎት የተሳለጠ እንዲሆን ለማስቻል እንደሚሰራም አስገንዝበዋል።
በምልከታቸው ወቅት በክፍተት የተለዩ ጉዳዬችን በየደረጃው ምላሽ ለመስጠት እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ እንደሚሰራም ዶ/ር ሳሮ ተናግረዋል።
በአጠቃላይ በክልሉ ካለፉት አመታት ጋር በንጽጽር ሲታይ የተሻለ ስራ የተያበት ዓመት መሆኑንም አንስተዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በበኩላቸው ክልሉ ከተመሠረተ ወዲህ ጥራት ያለው እና ፍትሃዊ የጤና አገ/ት ተደራሽ ለማድረግ የጤና ተቋማት ላይ በትኩረት መሰራቱን ተናግረዋል።
የጤና አገልግሎትን አሰጣጥን በማሻሻል የህብረተሰቡን የጤና መድህን አገ/ት ተጠቃሚነት፣ የጤና ቁሳቁስ ግብዓት የማሟላት ስራ እየተሰራ መሆኑን ያገለጹት አቶ ሳሙኤል በክልሉ በየአካባቢው የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቶች ግንባታ ስራ እና ሌሎች በርካታስራዎች እየተከናወኑ ስለመሆኑም አስረድተዋል።
ከመድኃኒትና ከጤና ቁሳቁስ ግብዓት አቅርቦት አኳያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት እንዲያስችል የማህሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ መቻሉን አውስተዋል።
የክልሉ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን ምንም እንኳን ክልሉ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም በህብረተሰብ ጤና ላይ በተለይም በህብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ ለውጥ የሚያመጡ ስራዎችን መስራት ተችሏል ብለዋል።
አቶ ማሙሽ ከኢንስቲትዩቱ ተልዕኮ አንዱ ጥራት ያለው የላብራቶሪ አገልግሎት ተደራሽ ከማድረግ ጋር ተያይዞ ከቀድሞ የደቡብ ክልል ሲወጣ የራሱ ላቦራቶሪ አገልግሎት ስላልነበረው በክልል ደረጃ የህብረተሰብ ጤና ላቦራቶሪ ለማደራጀት በትኩረት መሰራቱን አስረድተዋል።
በዝናሽ ደለለኝ