ብሔራዊ የተቀናጀ የጤና ስራዎች ዘመቻ በስልጤ ዞን ዞናዊ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በስልጢ ወረዳ ተጀመረ

  • Post last modified:May 19, 2025

በዞኑ ከ206 ሺህ በላይ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሚሆኑ ህፃናት የተቀናጀ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ መጀመሩን የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡ወራቤ፣ግንቦት 6/2017:-ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽንሀገር አቀፋዊ የኩፍኝ በሽታ መከላከያ ክትባት ዘመቻ ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆናቸውህፃናት በጤና ተቋማት ጊዚያዊ የክትባት መስጫ ጣቢያዎች ከግንቦት 6-10 ድረስ በዘመቻ መልክ ይሰጣል ተብሏል፡፡የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሸምሱ ከይረዲን ዘመቻውን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት ላይ እንደተናገሩት እንደ ሀገር መንግስት ለዘመቻው ከመቼውም ጊዜ በላይ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ለዘመቻው ስኬታማነት ባለፉት ጊዚያት ሰፊ የአቅም ግንባታ ስራ፣ ግብዓቶች ለሟሟላት እና ሌሎች አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱን አንስተዋል፡የኩፍኝ በሽታ የመከላከያ ክትባት ህፃናት በሽታውን የመከላከል አቅማቸው እንዲጨምር ብሎም በሌላ በሽታ እንዳይያዙ እና ጤነኛ እንዲሆኑ የሚያግዝ ነው ብለዋል፡፡በዚህ ዘመቻ ከ206 ሺህ በላይ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሚሆኑ ህፃናት የተቀናጀ የኩፍኝ ክትባት ተደራሽ ለማድረግ በዕቅድ ተይዟል ያሉት አቶ ሸምሱ ዘመቻ በሁሉም መዋቅሮች በዘመቻ መልክ ከግንቦት 6 እስከ 15 2017 ድረስ እንደሚሰጥም ጨምረው ገልፀዋል፡፡በመሆኑም ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን በአቅራቢያቸው በሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ የኩፍኝ ክትባቱን በማስከተብ የህፃናትን ህመምና ሞት እንዲሁም የአካል ጉዳት ለመቀነስ የጎላ ለመቀነስ በሚደረገው ጥረት የበኩላቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡የስልጢ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ካሚል ጃቢር የኩፍኝ በሽታ ህፃናትን ለሞት የሚዳርግ ብሎም ለከፍተኛ የአካል ጉዳት የሚያደርስ በሽታ ነው ሲሉም አስገንዝበዋል፡፡ከግንቦት 6/2017 ጀምሮ የተቀናጀ የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ ለማካሄድ ለህብረተሰቡ የግንዛቤ የማስጨበጫ ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ በዚህ ዘመቻ ላይ በወረዳው ከ24 ሺህ በላይ ህፃናት ተደራሽ ለማድረግ ግብ ተጥሏል ብለዋል፡፡በማስጀመሪያ መርሃግብሩ ላይ የተገኙት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ወልደሰንበት ሸዋ በበኩላቸው የኩፍኝ በሽታን ሙሉ በሙሉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለማጥፋት የተያዘውን ዘመቻ ውጤታማ ለማድረግ የክትባት መርሀ ግብሩ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደርጋል ባይናቸው።በክልሉ ከ1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ህፃናት የተቀናጀ የኩፍኝ ክትባት ተደራሽ ለማድረግ ያለመው ዘመቻ በዛሬው ዕለት መጀመሩን ጠቅሰዋል፡፡