አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ የግብ ስምምነት ተፈራረሙ

  • Post last modified:August 13, 2025

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ በተገኙበት የማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ግዛቸው ዋሌራ በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ የግብ ስምምነት ላይ ከሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር ተፈራርመዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ከጤና ፣ከትምህርት ፣ከመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ከሴቶችና ህጻናት ጉዳይ፣ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና፣ከወጣቶችና ስፖርት፣ከባህልና ቱሪዝም፣ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ፣ከአመራር አካዳሚ፣ከሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂቢሮዎች ጋር የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን