
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ከዞን ጤና መምሪያ ፕሮግራም ባለቤቶች፣ ከጤና ባለሙያዎች፣ ከላቦራቶሪ ባለሙያዎች፣ ከፖስታ አገልግሎት ድርጅት እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በቀሪ ወራት የቫይረስ መጠን ልኬት ለሚገባቸው ኤች አይ ቪ ታካሚዎች ሁሉ ተደራሽ ለማድረግ እና የምርመራ አገልግሎት ያላገኙ ኤች አይ ቪ ተጋላጭ ለሆኑ ጨቅላ ህጻናት የምርመራ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል የጋራ ውይይት መድረክ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
የክልል ጤና ቢሮ ሁሉ አቀፍ የኤች አይ ቪ ህክምና እና ክትትል ጥራት ለማሻሻል እንዲሁም ኤች አይ ቪ ከእናት ወደ ልጅ እንዳይተላለፍ ጨርሶ ለማስቆም በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የላቦራቶሪ ዳይሬክተር አቶ ግርማ ወንድሙ ውይይቱን በይፋ ባስጀመሩበት ጊዜ እንደተናገሩት ኤች አይ ቪ ኤድስ ዙሪያ የሚታዩ መዘናጋቶችን ለማስቀረት የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ያስፈልጋል።
ለዚህም የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ ተመርቆ በይፋ ሥራ መጀመሩ የተፋጠነ የምርመራ አገልግሎት ለመስጠት ሰፊ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል ዳይሬክተሩ።
በይፋ አገልግሎት መስጠት የጀመረው የክልሉ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ላቦራቶሪ በበቂ ባለሙያዎችና ዕቃዎች የተደራጀ መሆኑንም አንስተዋል።
ይህ ደግሞ ኤች አይ ቪ ኤድስና ሌሎች በሽተዎችን ምርመራ በማድረግ ቅኝትና ምላሽ ለመስጠት ያስችላል ነው ያሉት አቶ ግርማ ።
በክልሉ ጤና ቢሮ በዘርፈ ብዙ ኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዳይሬክቶሬት የኤች አይ ቪ ኤድስ ህክምናና ክትትል አማካሪ አቶ ታደለ ተሾመ ሰነድ አቅርበዋል።
በኤች አይ ቪ ህክምናና ክትትል ወቅት ወቅታዊ የሆነ የቫይረስ መጠን ልኬት የህክምና ስኬትንና የታካሚዎችን ጤንነት ለመከታታል ወሳኝ እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
ወይይቱ ለተከታታይ ሁለት ቀናት የሚቆይ ስሆን በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት የሚተገበሩ ስራዎች የድርግት መርሀ-ግብር እና ክትትል ስርዓት ሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በማዘጋጀት እና በመግባባት ወደ ትግበራ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡
በአብርሃም ሙጎሮ