
በክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊዎች የተመራ የማኔጅመንት ቡድን በሁለተኛ ቀን ውሎው በየመዋቅሩ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የዘመቻው አካል የሆነ ድጋፋዊ ምልከታ በሀዲያ ዞን አድርገዋል ፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በዞኑ እየተከናወነ የሚገኘውን ወቅታዊ የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አባላት የማፍራት የንቅናቄ ስራዎች የደረሰበትን አፈጻጸም ምልከታ አድርገዋል ፡፡
በዞኑ ዳምቦያ ወረዳ የሀብቾ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግምባታ አፈጻጸም የደረሰበትን ደረጃም ምልከታ አድርገዋል ፡፡
በመጨረሻም የጎምቦራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና አስተባባሪ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል ፡፡
የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህንን ጨምሮ ሌሎች የህዝብን መሰረታዊ የጤና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች ለማረጋገጥ መስራት እንደሚገባ አንስተዋል ፡፡
በቢሮ ምክትል ኃላፊዎች የተመራው የማኔጅመንት ቡድን በዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ድጋፍ እያደረገ በየደረጃው ለሚገኝ መዋቅር የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን እንዲሁም ተያያዥ የጤና ስራዎች አፈጻጸም ግብረ መልስ እየሰጠ በተለያዩ መዋቅሮች በመዘዋወር ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ፡፡
በአንድ ሳምንት በክልሉ የሚጠበቀውን የነባር አባላት እድሳት እንዲሁም አዲስ አባላት የማፍራት ዘመቻ የሚካሄድ ሲሆን ፣ የተሰበሰበ ሃብት ወደ ባንክ የማስገባት ስራ በስፋት በሁሉም መዋቅሮች እንደሚሰራ ይጠበቃል ፡፡

