ከክልሉ ጤና ቢሮ የተመራው ቡዱን ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የማህበረሳብ አቀፍ ጤና መድህን ተግበር ገምግሞ ግብረ መልስ ሰጠ ፡፡

  • Post last modified:December 25, 2025

በክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፋሲካ አለሙ የተመራው ቡዱን በሶስተኛ ቀን ድጋፉ በቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የማህበረሳብ አቀፍ ጤና መድህን አፈጻጸም በመገምገም ግብረ መልስ ሰጥቷል ።

በከተማ አስተዳደር ደረጃ እየተሰራ ያለው ጤና መዲን ተግበር የነዋሪውን አቅም መሰረት ያደረጋ የተለያዩ ደረጃ ክፍያ መረጃ በመለያት እየተሰረ ያለው ስራ አበረታች መሆኑን ጠቁመዋል።

ማህበረሰቡ የአመቱን ክፍያ በወቅቱ ለማጠናቀቅ እየሰረ ያለው ተግበር ጥሩና ለሌሎችም ትልቅ ተሞክሮ የሚሆን ተግበር በመሆኑ ሁሉ አቀፍ ተግባሩን አጣናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።

ጤና መዲን ለማህበረሰቡ ትልቅ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ልዩ ትኩረት ሰጥተው በርብርብ ልሰሩት ይገባል ብለዋል።

ሁሉም የጤና መድህን ተጠቃሚ ህብረተሰብ ክፍል 100% የፋዕዳ ማታወቂያ ባለቤት እንዲሆኑ ማድረግ እንደሚገባም አንስተዋል።

በግብረ-መልሱ ላይ የክልሉ ጤና ቢሮ ማኔጅመንት አባል አቶ ግርማ ወንድሙ የዞ የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ዶክተር ሸምሱ ረሺድ ፣ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ/ቅ/ጽ/ቤትና የፖለቲካ አቅም ግንባታ ዘርፍ አቶ ሁሴን አብደላን ጨምሮ የሀላባ ዞን ጤና መምሪያና የከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ማኔጀመንት አባላት ተገኝተዋል፡፡