
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ልማት እቅድና ኢኮኖሚ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የ2017ዓ/ም የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ይገኛል
የቢሮው የጤና ልማት እቅድ ዳይሬክሬት ዳይሬክተር አቶ አይሌ ለማ የ6 ወር አፈፃፀም ግምገማን ባስጀመሩበት ወቅት እንደተናገሩት በዘርፉ በተለይም ከዕቅድ ዝግጅትና ክትትል ፣የጤና መረጃ ስርዓት (Health Information system)፣ ከፕሮጀክቶች ክትትልና ግምገማ እንዲሁም የተለያዩ የጤና መሰረተ ልማት ግንባታዎች ክትትልና ግምግማ ጋር ተያይዞ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አስረድተዋል
በዚህ የስድሰት ወራት አፈፃፀም ግምገማ ዋና ዋና ተግባራት የስራ አፈፃፀምን በጥልቀት በመገምገም ጠንካራ ጎኖችን ማስቀጠልና ደካማ ጎኖች ሊያሻሽሉ የሚችሉ ቀጣይ አቅጣጫዎችንና ስትራቴጅዎችን ማስቀመጥ እንደሚገባ አሳውቀዋል፡፡
የሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች በተዘጋጀው ሰነድ መሰረት ሪፖርታቸውን በማቅረብ በቀረበው ሪፖርቶች ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል
በአፈፃፀም ግምገማው ከክልል ጤና ቢሮ የማኔጅመንት አባላት፣ የክልል ጤና ቢሮ የሚመለከታቸው ባለሙያዎች፣ ከሁሉም ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የጤና ልማት እቅድ ስራ ሂደት አስተባባሪዎች፣ የጤና መረጃ ባለሙያዎችና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ስራ ሂደት አስተባባሪዎች፣ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች፣ ከክልሉ ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ እና ከግል ጤና ተቋማት ማህበር ተወካይ ተሳትፈዋል፡፡
በነገው እለት የክልሉ ጤና ቢሮ የጤና ልማት እቅድና ኢኮኖሚ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዋና ዋና ተግባራት አፈፃፀምና በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በተለያዩ ፕሮግራሞች የሚከበረውን የጤና መረጃ ሳምንት (Health data week) አስመልክቶ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የሚካሄድበት ይሆናል፡፡
በሸምሲያ አደም