
ክልላዊ የመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ፎረም የቢሮው ማናጅመንት አካላት እና ባለሙያዎች የጤና ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሙያዎች በተገኙበት በይፋ መጀመሩም ታውቋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ የፎረሙ መመስረት የመድኃኒትና የህክምና ቁሳቁስ አቅርቦት አገልግሎት በተሳለጠ እና በተቀናጀ መልኩ ለመምራት አጋዥ መሆኑን አብራርተዋል።
ፎረሙ እንደ ክልል በይፋ መጀመሩን የተናገሩት አቶ ሽመልስ ትግበራውን እስከ ታችኛው መዋቅር በማውረድ ተፈጻሚ የሚደረግ መሆኑን በመጠቆም የፎረሙ መመስረት በሀገር አቀፍ ደረጃ የህክምና መገልገያ መሳሪያ እንዲሁም ከመድኃኒት አስተዳደር፣ አያያዝ ስርዓትና አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያችስል ተግባር እንደሆነ ገልጸዋል።
የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊና የህክምና አገልግሎቶች ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ፎረሙ የተመሰረተበት ዓላማ የመድሀኒት ሰንሰለት አስተዳደር ቅንጅትን በማሻሻል መሠረታዊ መድሀኒቶች እንዲሟሉና በተፈለገው ጊዜ መጠንና ጥራት እንዲኖር በማድረግ ለህብረተሰቡ ምላሽ የሚሰጥ ስርዓት መዘርጋት መሆኑን ገልጸዋል።
የመድሀኒትና ህክምና መገ/ያ መሳሪያዎች አስተዳደርን በማቀናጀት የመድሀኒት ብክነትና የህ/መገ/ያ መሳሪያዎች የቆይታ ጊዜን በመቀነስ የባለድርሻ አካላትን ዓቅም በማጠናከር የፋይናንስና ቴክኒካል እገዛዎችን በማድረግ የክልሉን የመድሀኒት አቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደርን ማማከርና ችግር ፈቺ ውሳኔ መስጠት እንደሚገባም ተናግረዋል።
የዘርፉ ማነቆዎችንና ክፍተቶችን መለየትና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ማመላከት ለዚህም የሚሆን የበጀትና ሙያዊ ድጋፍ ማድረግ ተገቢ ነው ያሉት አቶ ሳሙኤል በባለድርሻ አካላት መካከል የግንኙት ስርዓትን communication platform በመዘርጋት በመድሀኒት አስተዳደር እና አቅርቦት ላይ ያሉ ችግሮችን ማረም እንደሚገባ ተናግረዋል።
የማ/ኢት/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ