
በሳምንቱ ውስጥ የተከናወኑ የወባ ጫናን ጨምሮ ሌሎች 36 በሽታዎች ላይ ቅኝትና ምላሽ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ተደርጎባቸዋል ።
የቢሮዉ የጤናና ጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዳይ/ ዳይ/አቶ ወልደሰንበት ሸዋለም የዚህን ሳምንት ቅኝት ሲያብራሩ በሳምንቱ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀምና የግንዛቤ ስራዎችን በማጠናክር የወባ በሽታ ከባለፈው ሳምንት አንፃር መቀነሱን ጠቁመዋል።
እንደ አቶ ወልደሰንበት ገለፃ የወባ በሽታ ጫናዉ በጨመረባቸዉ አከባቢዎች ላይ መከላከልን መሠረት ያደረገ የክትትል እና የቁጥጥር ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም አሰረድተዋል
በክልል ደረጃ የወባ ጫና በሚፈለገዉ ልክ እንዲቀንስ እና በቀጣይ ስጋት ሆኖ እንዳይቀጥል የንቅናቄው ስራ እና ግንዛቤ የመፍጠር ተግባሩ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ዳይሬክተሩ አሳስበዋል ።
የስርዓተ ምግብ ጫና ያለባቸው አከባቢዎችን የልየታ ስራ በትኩረት መስራት ተገቢ ነዉ ያሉት ዳይሬክተሩ በምግብ እጥረት የተጎዱ ህፃናት የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ በልዩ ትኩረት መሰራት ያስፈልጋልም ብለዋል።
በክልሉ የክረምት ወራትን ተከትሎ የዉሃ ወለድ በሽታ እንዳይክስት ከውሃ ብክለት ጋር ተያይዞ የጤና ተቋማትን እና የህብረተሰቡን ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በክልሉ የክረምት ወራትን ተክትሎ ሊክሰት የሚችል የዉሃ ወለድ በሽን ለመከላከል ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አክባቢዎችን በመለየት እና የውሃ ብክለትን በመቆጣጠር ህብረተሰቡን ከኮሌራ በሽታ ቀድሞ መታደግ እንደሚገባም አንስተዋል።
በመድረኩም በክልሉ የወባ ወረርሽኝ እና በሌሎችም ጉዳዮች ዙሪያ በሳምንቱ ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በሸምሲያ አደም