
የቢሮው ሁሉም ዘርፍ ኃላፊዎች የ2018 በጀት ዓመት የውጤት ተኮር እቅድ ስምምነት ከቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ጋር ተፈራርመዋል።
የውጤት ተኮር እቅዱ በጤናው ዘርፍ ጥራቱን የጠበቀ፣ ፍትሐዊና ተደራሽ የሆነ ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ፓኬጅ በመስጠት እና በመቆጣጠር የህዝቡን ጤና ደህንነት መጠበቅ ነው።
የክልሉ ጤና ቢሮ የጤናውን ዘርፍ ለመለወጥ እና የዜጎችን ጤና ለማሻሻል፣ ጤናን የማበልጸግ፣ በሽታዎችን የመከላከል እና የፈውስ ህክምና ላይ በማተኮር በርካታ ሥራዎችን እየሰራ ይገኛል።
በክልሉ በጤናው ዘርፍ ለተመዘገቡት ውጤቶች የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃድ የላቀ ሚናና ለጤና ስርዓቱም መሠረት መሆኑ ተመላክቷል።
ቢሮው በበጀት ዓመቱ የእናቶች፣ ህጻናት፣ አፍላ ወጣቶች ጤና እና ስነ-ምግብ ማሻሻል፤ የበሽታዎች መከላከል እና ጤናን ለማጎልበት በትኩረት እንደሚሰራም ተገልጿል።
የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ በማሻሻል፣ ጥራት ያለው እና ፍትሐዊ የህክምና አገልግሎት ተደራሽነትን በማስፋት፤ የድንገተኛ ጤና አደጋዎች ቁጥጥር እና መልሶ በማቋቋም የህብረተሰቡን ጤና ለማሻሻል ከምንጊዜውም በላይ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተመላክቷል።
የውጤት ተኮር እቅዱን የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ፣ ህክምና አገልግሎት፣ ጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግብአት ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን፣ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና የጤና ሃብት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊዎች ናቸው የተፈራረሙት።
አብርሃም ሙጎሮ