የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃድ ውጤታማነት መረባረብ እንደሚገባ ገለጸ።

  • Post last modified:July 3, 2025

(ሆሳዕና ፡ሰኔ 26/2017 )የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በቡታጅራ ከተማ ያዘጋጀው የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃድ የንቅናቄ መድረክ ተጠናቋል።

የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃድ ውጤታማነት የሚያግዙ ሁለት ሰነዶች በማጠቃለያ መድረኩ ላይ ቀርበዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትልና የጤና ፕሮግራሞች ሃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ መድረኩን ሲያጠቃልሉ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃድ ውጤታማነት መረባረብ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የንቅናቄው መድረክ ከመዋቅር መዋቅር ልምድና ተሞክሮ መቅሰም ያስቻለና ውጤታማ እንደነበረ ገልጸዋል።

አቶ አሸናፊ የጤና ጣቢያ ሪፎርም ስራዎችን በአግባቡ በመረዳት መምራትና መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

የቢሮዉ ምክትል ሀላፊና የህክምና አገልግሎት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሀብቴ ገ/ሚካኤል በየደረጃው ማህበረሰቡን በማሳተፍ የጤናው ሴክተር ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ከመድረክ ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃድ ውጤታማ እንዲሆን ሙሉ አቅማቸውን እንደሚጠቀሙ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

የንቅናቄው መድረክ ዋና ዓላማ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃድ አገልግሎት አሰጣጥና ውጤታማነትን በዘላቂነት በማሻሻል ጥራት ያለው የጤና አገልግሎት በፍትሃዊነትና አካታችነት ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ መሆኑ የሚታወስ ነው።

በጁሲ ጥላሁን
ለተጨማሪ መረጃ