
ፍትሀዊና ጥራት ያለው የጤና አገ/ት ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል ሥርዓት ለመፍጠር በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገልጸዋል።
ሚኒስትሯ እና ሌሎች የፌዴራል የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ እና የቢሮ የማናጅመንት አካላት በተገኙበት በጉራጌና ሀድያ ዞኖች በጤናው ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎችን በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል፡፡
በዚህ ወቅት በክልሉ በሚገኙ የጤና ተቋማት እየተከናወኑ ያሉ የሥራ እንቅስቃሴዎችን በመመልከት ያሉ ጠንካራ ጎኖችንና ውስንነቶችን ለመለየት ያለመ የመስክ ምልከታ መሆኑን ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል ።
ሚኒስትር መ/ቤቱ ከህክምና አገልግሎት ጋር ተያይዞ ከማህበረሰቡና ከጤና ባለሙያዎች የሚነሱ ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ በመመለስ ጤናማና አምራች ዜጋን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።
የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ