የአለም አእምሮ ጤና ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል ።

  • Post last modified:February 7, 2025

በሥራ ቦታ ለአእምሮ ጤና ቅድምያ የምንሰጥበት ጊዜ ነው” በሚል መሪ ቃል የአለም አእምሮ ጤና ቀን ! በወራቤ ኮምፕሬሄንሲብ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዉስጥ መከበሩም ታውቋል።

አቶ ሌልሳ አማኑኤል የጤና ሚንስትር ሚንስተር ዴኤታ ከፍተኛ አማካሪ በዉይይት መድረኩ ላይ እንደተናገሩት ጤናማና አምራች ዜጋን ለማፍራት፣ ህብረተሰቡ ለአእምሮ ጤና ትኩረት እንዲሰጥ ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን በመስጠት እንዲሁም ጥራት ያለዉ የአእምሮ ህክምና አገ/ን ተደራሽነቱን ማስፋት ይገባል ብለዋል።

አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የማዕ/ኢት/ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ በአለም አእምሮ ጤና ቀን ተገኝተው እንደተናገሩት የአእምሮ ጤና እክል በየትኛውም የእድሜ ክልል ዉስጥ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚያጠቃ በሽታ ሲሆን የአስተሳሰብ እና የባህሪ ለዉጥ ሲኖር እንዲሁም ከተለመደው ትክክለኛ ፀባይ ዉጪ ሆነው ቀጣይነቱ ከተረጋገጠ ወደ ህክምና መስጫ ተቋም በመሄድ ምርመራዎችን ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

አቶ ሳሙኤል አክለዉም በክልሉ በ2016 ዓ/ም የአእምሮ የጤና ህክምና 23,650 ታማሚዎች ህክምና የተሰጣቸው ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ 74 በመቶ በስልጤ ዞን ባሉ ተቋማት አገልግሎቱን እንዳገኙ አስገንዝበዋል።

በክልሉ የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ብቻ በሙሉ አቅም የአእምሮ ህክምና አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።

ዶክተር ህይወት ሰለሞን የጤና ሚንስትር በሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ በፕሮግራሙ ላይ እንደገለፁት ሀገራችን የአእምሮ ጤናን አስጠብቆ ድህነትን እንድታሸንፍ የስራ ቦታዎችን ደህንነቱ የተጠበቀና ለአእምሮ ጤና የተመቸ እንድሆን በልዩ ትኩረት መስራት ይገባል ብለዋ።

ዶክተር ካሊድ ሸረፋ የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሀላፊ በበኩላቸው ሆስፒታላችን ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው አገ/መካከል አንዱ እና ዋነኛው የአእምሮ ህክምና አገ/ት ሲሆን የተገልጋይ ፍሰቱ ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ በመምጣቱ በ2016 ዓ/ም በተመላላሽ ህክምና አገልግሎት ብቻ ለ49,179 ለአእምሮ ሁሙማን አገልግሎት መሰጠቱን አስረድተዋል ።

በውይይት መድረኩ ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስቶ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል።

በመጨረሻም የስራ ሀላፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶች የሆስፒታሉን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

የማ/ኢት/ክ/መ/ ጤና ቢሮ