
የአለም የአዕምሮ ጤና ቀን”በሥራ ቦታ ለአዕምሮ ጤና ቅድሚያ የምንሰጥ ጊዜ ነው” በሚል መሪ ቃል የሚከበር መሆኑም ታውቋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፣ የስነ አዕምሮ የጤና ችግር በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ የሰው ልጆችን ሊያጠቃ የሚችል በሽታ መሆኑን ገልጸዋል።
ተከታታይነት ያለው የአስተሳሰብ እና የባህሪ ለውጥ እና ከበድ ያለ የአዕምሮ ጭንቀት ሲያጋጥም ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ እንደሚገባ የገለጹት አቶ ሳሙኤል የሥነ ልቦናና የማህበራዊ ድጋፍ መስጠት እንደሚገባ ተናግረዋል።
በክልሉ በሚገኙ ሆስፒታሎች የአእምሮ ጤና ችግርን ለመከላከል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊው የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሙሉ አቅሙ ህክምናውን እየሰጠ መሆኑን አመላክተዋል።
የስነ አዕምሮ ህመም የግንዛቤ ክፍተቶችን ለመቅረፍ የሚያስችል የግን እዛቤ ማስጨበጫ መስራት እንደሚገባ በመግለጽ ህብረተሰቡ ለአዕምሮ ጤናና ተጓዳኝ የሆኑ የጤና ችግር ለሚያስከትሉ ለሚችሉ ሱሶች ተጋላጭ እንዳይሆን እየተሰራ መሆኑንም አቶ ሳሙኤል አክለው ገልጸዋል።
በጤና ሚኒስቴር የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ህይወት ሰለሞን በበኩላቸው የአዕምሮ ጤና ችግር ከፍተኛ የጤና ችግር ከሚያስከትሉ በሽታዎች መካከል አንዱ መሆኑ ገልጸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ የሚያስከትል መሆኑን አስገንዝበዋል።
የአዕምሮ ጤና ጉዳይ በሁሉም ቦታ ሊከሰት የሚችል መሆኑን የጠቆሙት ወ/ሮ ህይወት ለአዕምሮ ጤና ችግር ማህበረሰቡን ከሚዳርጉ ችግሮች እራሱን እንዲጠብቅ በማድረግ፣ የጤና ችግሩ ሲያጋጥም ፈጥኖ ህክምና እንዲያገኙ ማድረግ ተገቢ እንደሆነ ገልጸዋል።
የወራቤ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ካሊድ ሸረፋ በበኩላቸው በሆስፒታሉ የአዕምሮ ጤና ህክምና እየተሰጠ መሆኑን ተናግረው የአዕምሮ ጤና ችግርን ለመቅረፍ በጋራ ቅንጅታዊ አሰራሩን ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል።
አቶ ሌልሳ አማኑኤል የጤና ሚንስትር ሚንስተር ዴኤታ ከፍተኛ አማካሪ ፣አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የማዕ/ኢት/ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ ፣፣ ዶክተር ህይወት ሰለሞን የጤና ሚንስትር በሽታ መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ ፣ ዶ/ር ካሊድ ሸረፋ የወራቤ ኮምፕሬሄንሲብ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስካያጅ፣ አቶ ጀማል ሽፋ የቅ/ጰ/ሚ/ሜ/ኮ/ሆስፒታል አስተዳደር እና ቢዝነስ ም/ፖሮቮስት፣ሀጂ መሀመድ ከሊል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ም/ቤት ፕሬዚዳንት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል።
የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ