የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በይፈ ተመረቀ ፡፡

  • Post last modified:December 25, 2025

የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቀደም ሲል በይፋ ሳይመረቅ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጠ የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አንተነህ ፋቃዱ ሆስፒታሉን በይፋ መርቀው ከፍተዋል።

ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አንተነህ ፈቃዱ ዛሬ በይፋ የተመረቀው የአንጋጫ ሆስፒታል በዘላቂነት የተሟላ አገልግሎት ለማህበረሰቡ እንዲሰጥ የተቋሙ ባለሙያዎች፣ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላትና የአከባቢው ማህበረሰብ በትኩረትና በየኔነት ስሜት ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።

ማህበረሰባችን ከዚህ ቀደምም ቢሆን ለትምህርትና ለጤና ተቋማት ሀብት ንብረቱን ሳይሰስት በማበርከት የሚታወቅ ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ለአንጋጫ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በበኩላቸው ክልሉ በአዲስ መልክ ከተዋቀረ ጀምሮ በሁሉም የልማት ዘርፍ ብዙ ስኬታማ ሥራዎችን ስለመስራቱ ጠቅሰው በጤናውም ዘርፍ ከክልል ጀምሮ እስከ ቀበሌ የጤና ስርዓትን የማጠናከር ላይ ያተኮረ ሥራዎችን በመሥራት የማህበራዊ ስራዎችን ማጠናከሪያ አንዱ ዘርፍ በመሆኑ ሰፋፊ ሥራዎች እየተሰራ ስለመሆኑ ገልፀዋል።

ለረዥም ዓመታት በማህበረሰብ ዘንድ ማነቆ የሆኑ ችግሮችን ከሥር መሠረታቸው ለይቶ በማውጣት፣ የአጭር የመካከለኛ እና የረዥም ጊዜ የድርጊት መርሐ ግብር በማዘጋጀት በተለይም የእናቶች እና የህፃናት ጤናን በማሻሻል ማህበረሰቡ የራሱን ጤና የሚያበለጽግበት እና ዘላቂና አስተማማኝ የጤና ሥርዓት ለመፍጠር ታቅዶ ስሰራ መቆየቱን ገልጸው በህደቱም ተስፋ ሰጭ ውጤቶች ስለመመዝገባቸው ተናግረዋል።

የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አረጋ እሸቱ በበኩላቸው የህብር፣ የአንድነት እና የትብብር ተምሳሌት ለመሆኑ የህዝቡ ታሪክ እንደ መነሻ የሚጠቀሰው የሀምበርቾ ተራራ አንድ ግዙፍ እና አንድ ወጥ ሆኖ የሚታየው የትልቅነቱ እና የግዝፈቱ ምስጥር ሰባቱንም ተራሮች አቅፎ መያዙ እንደሆነ እና መደማመጥ ፣ በመተባበር እና አንድነት ፋሽኑ የማያልፍ የማያረጅ ሁሌም ለአሸነፊነት የሚያበቃ ትልቅ ጉልበት ነው ብለዋል።

በሀገራችን ኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞ በጀመረችበት የጉባ ብሥራቶች በአራቱም የሀገራችን ጫፎች በተስተጋቡበት በዚህ ጊዜ የሚመረቀው የአንገጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የዞናችን የማንሰራራት ጉዞ ጅማሬ ከሚያመላክቱ መገለጫዎች አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

ሆስፒታሉ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ለህብረተሰቡ እንድሰጥ የሁላችንም ተሳትፎ ወሳኝ ነው ያሉት የተከበሩ አቶ አረጋ እሸቱ በቅርቡ የበጎ አሳቢዎችን ፈጣኝ ምላሽ የሰጡ፣ ሀብት ያሰባሰቡ አካላትን እና ድጋፍ ያደረጉትን በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭ ያሉ የዞኑ ተወላጆች እና ወዳጆችን አመስግነው ሁስፒታሉ አሁንም ሙሉ አገልግሎት እንድጀምር ሁሉም ባለድርሻ የጀመሩት ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር የሜዲካል አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ እና ተወካይ ዶክተር ኢልባቦር ቡኖ፣ ሆስፒታሉ ለምረቃ ስበቃ አልጋ በአልጋ አልነበረም ፕሮጀክቱ የፌዴራል እና የክልል መንግሥት ቅንጅት የተሰራ ስለመሆኑ ገልፀው ተቀናጅተን እና ተግባብተን ከሰሜን ውብ የሆነ ሥራ መሥራት እንደሚቻል ሆስፒታሉ ማሳያ ነው ብለዋል።

መንግሥት ጤናን እንደ መሠረታዊ መብት በመቀበል ዜጎች በሚኖሩበት ቦታ ሁሉ ፍትሃዊ ጥራት ያለው ተመጣጣኝ የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ በጽናት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅሰው የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

የአንጋጫ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ዘርሁን ተክሌ የአንጋጫ ከተማ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በአሁግ ወቅት በውስጡ ሰባት ሀክሞችን ጨምሮ ከ170 በላይ የጤና ባለሙያዎች ተቀጥረው ሥራ ጀምረዋል ብለዋል።

በጤናው ዘርፍ የህብረተሰብ ተሳትፎ ወሳኝ ነው ያሉት ከንቲባው ከ40 ሚሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ በሚደንቅ ተሳትፎ የገንዘብና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሉዋል ነው ያሉት።

በዕለቱም የአንገጫ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር ሁሉም ቀበሌያት የሰንጋ እና የሙክት ስጦታ ያበረከቱ ሲሆን የከምባታ ዞን አስተዳደርን ጨምሮ የተለያዩ ተቋማት የገንዘብ እና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

በምረቃ መርሐ ግብር ላይ ፣ የፌዴራል ጤና ሚኒስተር ተወካዮች ፣ የክልል ቢሮ ምክትል ኃላፊዎች ፣ የከምባታ ዞን ዋና የመንግስት ተጠሪ እና የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ተክሌ ስዩም የከምባታ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ረመቶ አቦ፣ የከምባታ ዞን አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት የአንጋጫ ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር አመራሮች የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል።