
ሰኔ 19/2017 ዓ.ምበሆስፒታሉ ለመጀመሪያ ጊዜ አንዲት ነፍሰጡር እናት ሙሉ የቀዶ ህክምና ተደርጎላት በሙሉ ጤንነት ላይ እንደምትገኝም ሆስፒታሉ አስታውቋል ።የአገና የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ስራስኪያጅ አቶ ጥላሁን ሀይሌ እንደገለፁት ይህ ህክምና እስካሁን ሂደት በሆስፒታሉ ባለመጀመሩ ማህበረሰቡ በተለያየ መልኩ እንዲጎዳ አድሮጎታል ብለዋል።የህክምና ክፍሉ መሳሪያ እንዲሟሉ በተለይም የወረዳው መንግስት ፡ ጋበር በጎ አድራጎት ድርጅት ትልቁን ድርሻ የሚይዙ ናቸው ያሉት ስራስኪያጁ ለዚህም የህክምና መሳሪያ ከ4.7 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸዋል ብለዋል ።በሆስፒታሉ አሁን አስፈላጊ የሆነው የራጅ /የX-ray/ አገልግሎት ተጠቃሽ መሆኑን ያመላከቱት ሀላፊው በቀጣይም መንግስት ከማህበረሰቡ ሰፊ ውይይት በማድረግ የህክምና መሳሪያው ተገዝቶ ለማህበረሰቡ ተጨማሪ አገልግሎት ለመስጠት ርብርብ ይደረጋልም ብለዋል።ሆስፒታሉ ቀጣይ በዚሁ ከቀጠለ ባለሙያዎች ልምዳቸው በማዳበር ለማህበረሰቡ የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ሰፊ እድል የሚፈጥርም ነው ያሉት አቶ ጥላሁን እስካሁን አገልግሎት እየተሰጠበት ያልነበረው የቀዶ ህክምና ዘርፍ ዛሬ አገልግሎት መስጠቱ እጅግ ደስታ የሚፈጥር በመሆኑ ለመላው ማህበረሰቡ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ክፍል ሀላፊ ዶ/አትናድ ይርጋ ከዚህ በፊት በህክምናው መሳሪያ እጥረት ምክንያት ብቻ ማህበረሰቡ እዚሁ ማግኘት ያለበት አገልግሎት ማግኝት ባለመቻላቸው የተለያየ እንግልት እንዲኖር ከማድረጉም በተጨማሪ ሪፈር ሲደረጉ በሚወስደው ጊዜ ምክንያት በተጨማሪ የተቋማት ጫና እየፈጠር ቆይቷል ብለዋል።በዛሬው እለት የጀመረው አገልግሎት ለማህበረሰቡ የምስራች ነው ያሉት ዶ/ር አትናድ ይህም እንዲሆን ትልቅ ርብርብ ያደረጉት የእዣ ወረዳ መንግስት እና ጋበር በጎ አድራጎት ድሮጅት አመስግነው በቀጣይም በሆስፒታሉ የግድ የሚያስፈልጉ እንደነ የX-ray ማሽንና ሌሎችም ተጨማሪ የሆኑ አስፈላጊውን ግብዓቶች እንዲሟሉ ማህበረሰቡን በማሳተፍ ጥረታቸው አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አድርገዋል። በሆስፒታሉ የማህፀን ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ሰብስቤ ለማ ከዚህ በፊት በሰርጀሪ የሚወልዱ እናቶች ሲገጥሙ ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሪፈር እንደሚደረጉ አስታውሰው በዛሬው እለትም አንዲት ወላድ እናት በሆስፒታሉ ደረጃ ያለምንም ችግር በቀዶ ህክምና በሰላም እንድትገላገል መደረጉንም ገልፀዋል ።በቀጣይም በተሟላ መልኩ በቀዶ ህክምና ማዋለድን ጨምሮ ማንኛውንም ማህፀንና ችግር ያለባቸው እናቶች አገልግሎት በሆስፒታሉ ደረጃ ተገቢውን አገልግሎት እንደሚሰጥም ዶ/ር ሰብስቤ አክለው ገልፀዋል ።በሆስፒታሉ የተናጀ ድንገተኛ ቀዶ ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር እንቁ ካሳ በበኩላቸው አንድ ሆስፒታል በጣም ከሚያስፈልጉ ነገሮች ውስጥ የኦፕሬሽን አገልግሎት መስጠት ትኩረት ከሚሹ ነገሮች ተጠቃሽ መሆኑን ገልፀው ይህንን ችግር በመረዳት የወረዳው መንግስት ፡ ጋበር በጎ አድራጎት ድርጅት የህክምና መሳሪያ እንዲሟላ በማድረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአንዲት እናት ሌላ ቦታ ሳትገላታ በሰላም እንድትገላገል የህክምና አገልግሎት በመስጠታችን እጅግ ደስ ያሰኛልም ብለዋል።በሆስፒታሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በቀዶ ህክምና በሰላም ለተገላገለችው እናት የተለያዩ ስጦታዎች አበርክቶላታል።በዛሬው እለት በሙሉ ቀዶ ህክምና የተገላገለች እናት እሷንም ልጇን ሙሉ ጤንት እንደሚሰማቸው በመግለፅ ሌላ ቦታ ሳትሄድ እዚሁ አቅራቢያቸው በሚገኘው ሆስፒታል በሰላም በመገላቸው ደስተኛ መሆኗንና ሆስፒታሉም ላበረከተላት ስጦታና ላደረገላት ልዩ እንክብካቤ ምስጋናዋን አቅርባለች ፡፡የዞኑ ጤና መምሪያ