
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የእናቶች ጤና አገልግሎት አፈጻጸም ግምገማና የእናቶች ጤና ማስፈጸሚያ ሰነዶች ማስተዋወቂያ መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።
በክልሉ ጤና ቢሮ የእናቶችና ህጻናት ጤና እና ሥርዓተ ምግብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሌጅሶ በዚህ ጊዜ እንዳሉት፦ የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ሞት ለመቀነስና ጤና ለማሻሻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መሥራት ይገባል።
አቶ ተስፋዬ፦ ሁለተኛ ዙር የጤና ሴክተር የኢንቨስትመንትና ጤና ልማት ዕቅድ የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ሞት ለመቀነስ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል ነው ያሉት።
እንደ ሀገር በ2030 ላይ የእናቶችና የጨቅላ ህጻናት ሞት ቁጥር ለመቀነስ ግብ ተጥሎ እየተሰራ እንደሆነ አንስተዋል።
አንዲት እናት ጤናዋ ተጠብቆ ልጅ መውለድ እንድትችል ሁኔታዎች መመቻቸት አለባቸው ሲሉም ተደምጠዋል አቶ ተስፋዬ።
እናቶች ከእርግዝናቸው በፊት የጤና ችግሮች ካለባቸው ተመርምረው ህክምና በመውሰድ የቅድመ እርግዝና ክትትል ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል።
የእናቶች ጤና ማስፈጸሚያ ሰነዶች ቀርቦ ማስተዋወቂያና ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች ባነሱት አስተያየት፦ በጤናው ዘርፍ ማነቆ ሆኖ የቆየውን የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ሞት ለመቀነስ በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።
አብርሃም ሙጎሮ