
(ሆሳዕና ፣የካቲት 23/2017) የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር መቅደስ ዳባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ የእንጃፎ መሰረታዊ ጤና ኬላ እና ሞዴል የቤተሰብ መንደር ምልከታ አድርገዋል
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ በጤና ኬላዎች እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት እና ተዛማጅ ተግባራት ምልከታ ባደረጉበት ወቅት እንደገለጹት የክልሉ መንግስት ለጤናው ዘርፍ በሰጠው ልዩ ትኩረት የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ አስችሎታል ብለዋል።
በክልሉ በጤና ክብካቤ ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ሲሉም ጠቁመዋል።
የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች በእናቶችና ህጻናት ጤና ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት እያከናወኑት ያለው ስራ ውጤታማ ነው ብለዋል።
መንግስት በመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ ስራ ላይ በማተኮር እየሰራ መሆኑን ሚኒስትሯ አብራርተዋል።
የክልሉ መንግስት በሁለት ዓመታት ውስጥ አጠቃላይ ጤና ኬላዎችን በስፋት በመገንባት የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የጀመራቸው ስራዎች ስኬታማ ናቸው ብለዋል።
በሚኒስትሯ የተመራ ልኡክ በሆሳዕና ከተማ በንግስት እሌኒ መሐመድ መታሰቢያ ኮምፕሬንሲፍ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የመስክ ምልከታ እንደሚያደርግ ተጠቁሟል።
የክልሉ መ/ኮ/ጉ/ቢሮ