የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በጤናው ዘርፍ የሚሰሩ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በበጎ ፈቃድ ደም በመለገስ አስጀምረዋል ፡፡

  • Post last modified:July 2, 2025

በክልሉ ጤና ቢሮ በክረምት ወራት በጤናው ዘርፍ የህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች በማቀድ ወደ ስራ ተገብቷል ፡፡

የቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በበጎ ፈቃድ ደም በመለገስ ያስጀመሩት ሲሆን በክረምቱ ጤና ተቋማትን ጽዱ እና አረንጓዴ ማድረግን ፣ ጨምሮ በሌሎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎቶች የጤናው ዘርፍ አመራር እና ባለሙያ ይሳተፋል ብለዋል ፡፡

በክልሉ ጤና ቢሮ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አማካኝነት 5500 ዩኒት ደም መሰብሰብ ፣ 150,000 ሺ ችግኞችን በጤና ተቋማት መትከል ፣ ጽዱ የጤና ተቋማትን መፍጠር ፣ 50,000 ነጻ ምርመራ እና ህክምና መስጠት ፣ የወባ እና ኮሌራ በሽታ መከላከል እና ቁጥጥር ስራዎችን ጨምሮ ሌሎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችን ለመስጠት ኦየተሰራ ይገኛል ፡፡

በዚህም ከ7ሺ በላይ የጤና ባለሙያዎች የሚሳተፉ መሆኑ ታውቋል ፡፡

በበጎ ፈቃድ ደም ልገሳው የጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አቶ ሀብቴ ገብረሚካኤልን ጨምሮ የቢሮ ማኔጅመንት እና ሌሎች በጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ተሳትፈዋል ፡፡

በቢኒያም ገዙ
ለተጨማሪ መረጃ
telegram https://t.me/centralethiopiarhb
website
https://cerhb.gov.et/