
መድረኩ የተሰሩ ስራዎች አፈጻፀም የሚገመገሙበት እና ተግዳሮቶችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ የሚቀመጥበት መሆኑን የገለጹት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፤ 2017 በጤና ዘርፍ አበረታች ውጤቶች የተመዘገቡበት እንዲሁም ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንድንጠነክር ያደረጉ እና ልምድ የተገኘባቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
2017 የጤና ፖሊሲዎችን ለመተግበር የሚያስችል የጤና አዋጅ የጸደቀበት መሆኑን ያስታወሱት ዶ/ር መቅደስ፤ በቀጣዩ አመት የሪፎርም ትግበራ ላይ ትኩረት በመስጠት እንደሚሰራ አስረድተዋል፡፡
በመድረኩ የ2017 ዓ.ም ሪፖርት ለዉይይት የቀረበ ሲሆን የጤና ሚኒስቴር፣ የክልል ጤና ቢሮ ሃላፊዎች እንዲሁም ተጠሪ ተቋማት እና የፌደራል የሆስፒታል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
መረጃው የጤና ሚንስትር ነው ፡፡