የጤና ሚኒስትሯ መቅደስ ዳባ (ዶ/ር )በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወልቂጤ ጤና ጣቢያን አገልግሎት አሰጣጥ ምልከታ እያደረጉ ነው

  • Post last modified:March 3, 2025

(ሆሳዕና፤ የካቲት 23/2017 የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ እና ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የወልቂጤ ጤና ጣቢያ የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ምልከታ እያደረገ ይገኛሉ።

ሚኒስትሯ እና በእርሳቸው የተመራ ልኡክ በወልቂጤ ጤና ጣቢያ የነፍሰ ጡር እናቶች ማቆያ ፣የድህረ ወሊድ፣ የህክምና፣የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም እንዲሁም በጤና ጣቢያው በተለያዩ የስራ ክፍሎች እየተሰጠ ያለውን አገልግሎት ተመልክተዋል።

ሚኒስትሯ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የወልቂጤ አጠቃላይ ሆስፒታል ጉብኝት አድርገዋል።

በመርሐ ግብሩ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አብዱልቃድር ገልገሎ(ዶ/ር )፣ የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ደረጄ ዱጉማ (ዶ/ር )፣ የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድርን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።።

የክልሉ መ/ኮ/ ጉዳዮች ቢሮ