
የጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ በስሩ ካሉ ሶስት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሮች ጋር የ2018 በጀት አመት ውጤት ተኮር እቅድ ላይ የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል ፡፡
አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ የግብ ስምምነት በተፈራረሙበት ወቅት እንደተናገሩት በተጠናቀቀዉ 2017 በጀት ዓመት የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ይበልጥ በማጎልበትና በ2018 በጀት ዓመት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አንስተዋል ።
የውጤት ተኮር እቅዱን የተፈራረሙት የእናቶችና ህፃናት ጤናና ስርዓተ ምግብ አገልግሎት ፣ ዘርፈ ብዙ ኤችአይቪ ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር እንዲሁም በሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ዳይሬክቶሬቶች ናቸው ።
በሸምሲያ አደም