
የጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የህክምና አገልግሎቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብቴ ገብረሚካኤል በስሩ ካሉ ዳይሬክቶሬቶች ጋር የ2018 በጀት አመት ውጤት ተኮር እቅድ ላይ የግብ ስምምነት ተፈራርመዋል ፡፡
አቶ ሀብቴ የግብ ስምምነት በተፈራረሙበት ወቅት እንደተናገሩት በዘርፉ ያሉ ዳይሬክተሮች ዛሬ በተፈራረምነው የእቅድ ግብ ስምምነት ላይ በስራቸው ካለው ፈጻሚ እና ባለድርሻ አካላት ጋር በተገቢው በመቀናጀው ለውጤታማነቱ መትጋት ይገባል ብለዋል ፡፡
የተፈረመው የእቅድ ግብ ስምምነትን በተገቢው በመፈጸም በ2017 በጀት ዓመት የተመዘገቡ የህክምና አገልግሎቶች ማሻሻል ስራዎችን በተሻለ ደረጃ ለማሻሻል ያስችላል ብለዋል፡፡
አቶ ሀብቴ ገብረሚካኤል የውጤት ተኮር እቅድ ግብ ስምምነቱን ከህክምና አገልግሎቶች ፣ ከመድሃኒት እና ህክምና መሳሪያዎች ዳይሬክቶሬቶች እና ከጤና ሀብት አሰባሰብ ኬዝ ቲም አስተባባሪ ጋር ተፈራርመዋል ።
በቢኒያም ገዙ