የጤና ፋይናነስ ስርዓት አቅምን ለማሳደግ እና የተለያዩ የአሰራር ቴክኖሎጂዎችን ወደ ስራ ለማስገባት ዓለም አቀፍ ልምዶችን ወደ ሀገራችን ማምጣት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

  • Post last modified:February 7, 2025

ሁሉን አቀፍ የጤና ፋይናንሲንግ በኢትዮጵያ ተግባራዊ ለማድረግ የጤና አገልግሎት ፍትሀዊነት ጥራት እና ተደራሽነት ማረጋገጥ ላይ ለመስራት የጤና ፋይናንሲንግ አቅምን ማሳደግ እንደሚገባ ተገለጸ።

የጤና ፋይናንስን ለማሻሻል የሚያግዝ የአቅም ግንባታ መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ዶክተር አስናቀ ዋቅጅራ በጤና ሚኒስቴር የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈጻሚ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ እንደተናገሩት በሀገራችን ያለውን የጤና ፋይናነስ ስርዓት አቅም ለማሳደግ እና የተለያዩ የአሰራር ቴክኖሎጂዎችን ወደ ስራ ለማስገባት አንዲቻል ዓለም አቀፍ ልምዶችን ወደ ሀገራችን ማምጣት፣ ተግባራዊ ማድረግ እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ ባለሞያዎች ብቃት እና ክህሎት ያላቸው፣ ተገቢውን ቴክኖሎጂ የመጠቀም አቅም ያዳበሩ ባለሞያዎችን ለማፍራት ከምክክር መድረኩ ብዙ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ዶክተር አስናቀ ዋቅጅራ ጥራት እና ተደራሽነትን ለማሳደግ በፍኖት ፕሮጀክት ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተሰሩ ጥናቶች በሚጠቁሙት መሰረት ለውጥ አምጪ ስራዎችን ለመስራት የባለሞያዎች አቅም ግንባታ እና የፋይናንስ ዘርፉን መዋቅር የማጠናከር ስራ በመረጃ ላይ የተመሰረት የፋይናስ ውሳኔ አሰጣጥ ስርአት ከመዘርጋት አንጻር የጤና ሚኒስቴር በዘርፉ ተስፋ ሰጪ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ
የጠቆሙት ዶክተር አስናቀ በቀጣይም የዘርፉ ባለሞያች ዓለም አቀፍ ልምዶችን ወደ ሀገራችን በማምጣት ለዘርፉ መጠናከር የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሲስተር ትዕግስት ተፈራ በኦሮሚያ ክልል በአሁኑ ወቅት ያለውን የጤና ፋይናንስን ለማሻሻል የተሰሩ ስራችን አንስተው ዘርፉን በእውቀት እና በአቅም ላይ የተመሰረት እንዲሆን ለማድርግ እንዲሁም የጤና ፋይንስ አሰራርን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ጠቁመው ለዚህም የጤና ሚኒስቴር እና የአጋር ድርጅቶች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር ጴተር ቤርማን በበኩላቸው የጤና ፋይናንስን ለማሻሻል በግልጽ በመነጋገር በአለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የጤና ፋይናንስን ልምድ ለጤናው ዘርፍ መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን አንስተው በኢትዮጰያ ያለው የጤና ፋይናንሲንግ በመንግስት እና በአጋር ድርጅቶች የሚሸፈን በመሆኑ የጤና ፋይናንስን ለማሻሻል አለም አቀፍ ልምዶችን መቀመር እና በትኩረት መስራት እንዲቻል ዘርፉ በሚፈልገው እውቀት ታግዞ ማከናወን ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በዚህ መድረክ የጤና ፋይናንሲንግን ተግባራዊ ከማድረግ አኳያ በሀገራችን ያለውን የማዋቅር እና የሰው ሀይል አደረጃጀት ምን እንደሚመስል የሚዳስስ ጥናት በአስራ አራቱም ክልሎች ባሉ የጤና ፋይናንስ፣ እቅድ እና ክትትል የስራ ክፍሎች ላይ እንዲሁም በፌዴራል ደረጃም በተመረጡ ስድስት የጤና ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት ላይ የጤና ሚኒስቴር ከፍኖት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር የዳሰሳ ጥናት የተሰራ ሲሆን የጤና ፋይናንስ እንዴት እንደተደራጀ፣ ምን ያክል የሰው ኃይል አለው ምን ምን ስራዎችን ያከናውናሉ፣ የጤና ስራዎችን ለመስራት ያላቸው ሞያዊ እውቀት በሚመለከት እና ስራዎችን በሚሰሩበት ግዜ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ይሰራሉ ወይ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መነሻ በማድርግ የተሰራው ጥናትም በመድረኩ ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ተገልጿል፡፡