
ርዕሰ መስተዳድሩ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን ያወያዩት ክልሉ ባዘጋጀው አመታዊ የጤና ኤክስቴንሽን ፌስቲቫል ላይ ተገኝተው ነው፡፡
አምራች ኃይል ለመፍጠር የዜጎችን ጤና መጠበቅ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን እንደሚገባም ነው ርዕሰ መሥተዳድሩ የተናገሩት፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ባስተላለፉት መልዕክት በያሉበት አካባቢ ህብረተሰቡን በተገቢው እንዲያገለግሉ አሳስበዋል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በዚህ ወቅት እንዳሉት የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ለማሻሻል ከምን ጊዜም ይልቅ ፖሊሲዎች ተቀርፀው እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የጤናው ሴክተር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት ይፈልጋል ያሉት ሚኒስትሯ የዜጎችን ጤና ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ፕሮግራሞች ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል፡፡
እንዴ ጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች አስተያየት እንዲህ ያለ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ፌስቲቫል ከረጅም ጊዜ በኋላ በመደረጉ ደስተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በዘርፉ የበለጠ ለውጥ እንዲመጣ በሙያ የበቁ የወንዶች ቁጥር እንዲጨመር ያነሱት የጤና ኤክስቴንሽኖቹ የትምህርት ዕድልና ጤና ዘርፍ ላይ የሚታዩ ችግሮች እንዲቀረፉ ጠይቀዋል፡፡
የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ለውይይት የሚሆን ሰነድ አቅርበዋል፡፡
የማ/ኢት/ክ/ጤና ቢሮ