በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህብረተሰብ ጤና ላይ የድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ስራ አፈጻጸም ተገመገመ ፡፡

በክልሉ በበሽታዎች ላይ በተደረገ ሳምንታዊ የቅኝት እና ምላሽ ስራዎች ሪፖርት ላይ ውይይት ተካሂዷል ፡፡
ወባ እና ኩፍኝን ጨምሮ በተለያዩ 17 በሽታዎች ላይ የተካሄደ ቅኝት እና ምላሽ ስራዎች አፈጻጸም በዞኖች በልዩ ወረዳ ደረጃ እንዲሁም በክልሉ ባሉ ጤና ተቋማት ደረጃ ያለበት ስርጭት እና የተከናወኑ ምላሾች በዝርዝር ተገምግሟል ፡፡
ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝት እና ምላሽ ስራ ፈጣን እና ጥራት ያለው የመረጃ ልውውጥ ማጠናከር ፣ በተደረጉ ቅኝቶች የተገኙ መረጃን ጥቅም ላይ ማዋል ፣ ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ፣ የመደበኛ ክትባት ተደራሽነትን ማሳደግ እምደሚገባ ከተሳታፊዎች ተነስቷል ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቱትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ በማጠቃለያው እንደገለጹት የክልሉ የወረርሽኝ ቁጥጥር ስራዎች በየጊዜው እየተሻሻለ መምጣቱን ገልጸዋል ፡፡
ወረርሽኝ ለመከላከል መደበኛ የክትባት እና የጤና ልማት ስራችንን በቅንጅታዊ አሰራር መፈጸም ይገባል ብለዋል ፡፡
በሚደረጉ ቅኝቶች የተገኙ መረጃዎችን መነሻ በማድረግ የመደበኛ የጤና ስራዎችን አጠናክሮ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል የህብረተሰብ ጤና ኢንስቱትዩት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ለገሰ ጼጥሮስ በበኩላቸው በሚደረጉ ቅኝቶች የምላሽ አሰጣጥ እና የክትትል ስራ ይጠናከር ብለዋል ፡፡
በክልሉ በአንዳንድ ዞኖች እና ልዩ ወረዳ የሚታዩ ክፍተቶችን በቅኝቶች በሪፖርቶች እና በድጋፎች ችግር ያለባቸው መዋቅሮች በልዩ ሁኔታ ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ለአስቸኳይ ግብረመልስ ተዘጋጅቶ ለሚመለከታቸው ተደራሽ እንዲሆን ተወስኗል ፡፡
በቢኒያም ገዙ