በክልሉ ጤና ቢሮ ጤናና ጤና ነክ አገልግሎቶች እና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት የጤና ቁጥጥር ስራዎች ለማሻሻል ከባለድርሻ አካላት ጋር የንቅናቄ መድረክ በወልቂጤ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው ፡ ፡

  • Post last modified:March 23, 2025

በመድረኩ የመክፈቻ እና የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ካስተላለፉት መልዕክቶች ዋና ዋናዎቹ

መንግስት ሁለንተናዊ ብልጽግናን በማረጋገጥ ጤናው የተጠበቀ አምራች እና ብቁ ዜጋ ለማፍራት በልዩ ትኩረት በርካታ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

በክልሉ በባለፉት ስምንት ወራት በጤናው ዘርፍ በርካታ ተግባራት በአመራር ትኩረት አግኝተው መመራታቸው ተስፋ ሰጪ ውጤቶች መታየቱ አያይዘው ገልጸዋል ፡፡

በክልሉ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ከማረጋገጥ ጎን ለጎን የአገልግሎት ጥራት ማሻሻል እና ማስጠበቅ ለማህበራዊ ብልጽግናችን ወሳኝ በመሆኑ በየደረጃው ካለ የሴክተር አመራር እና ባለሙያ የሚጠበቅ ሌላው ተግባር መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡

የጤና አገልግሎት ጥራት ለማረጋገጥ አገልግሎትን ስታንዳርዳይዝ ማድረግ እንደሚገባ አንስተው ለዚህ ውጤታማነት የዘርፉን ቁጥጥር ስርዓት እና ቅንጅትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል ፡፡

የክልሉ የጤና ቁጥጥር ስራዎች አበረታች ቢሆኑም በተቀመጠ በዝቅተኛ መስፈርት ከመስራት ፣ የጤና ተቋማት ንግድ ፈቃድ አሰጣጥ ተቀናጅቶ ከመስራት ላይ የሚታዩ ውስንነቶች ለመሻገር ታሳቢ ያደረገ መድረክ መሆኑን አቶ ሳሙኤል አስታውቀዋል ፡፡

ህዝባችን ደህንነቱ እና ጥራቱ የጠበቀ ምግብ ፣ መድሃኒት እና የጤና አገልግሎት ያስፈልገዋል ያሉት አቶ ሳሙኤል መንግስት ከአገልግሎት ሰጪው ባሻገር እየሰጠ ያለው አገልግሎት ሁለንተናዊ ጥራቱ የጠበቀ እንዲሆን እስከታች የተቆጣጣሪ መዋቅር በማደራጀት ጥራት ለማስጠበቅ ቁርጠኝነቱን በተግባር ማሳየቱን ገልጸዋል ፡፡

ውጤታማ ተግባር ለመፈጸም በየደረጃው ያለን የተቆጣጣሪ አካላት የመንግስትን ቁርጠኛ አቋም መሬት በማስነካት በተግባር ማረጋገጡን በትልቅ ኃላፊነት እና ትጋት እና በታማኝነት እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል ፡፡

ለመድረኩ በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ በክልልእና ፌደራል ቢሮ ኃላፊዎች እየቀረበ ይገኛል ፡፡

በመድረኩ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ምክትል ርዕሰመስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፍቃዱ ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ረዳት የመንግስት ተጠሪ እና የፖለቲካ እና ርዕዮት አለም ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይሁን አሰፋ ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ረዳት የመንግስት ተጠሪ እና የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ይግለጡ አብዛ ፣የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ፣ የር/መ/ር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ልዩ አማካሪ አቶ ንጉሴ አስረስ ፣ የቢሮ ምክትል ኃላፊዎች ፣ የዞን እና የልዩ ወረዳ አስተዳዳሪዎች እና ኃላፊዎች ተገኝተዋል ፡፡

በቢኒያም ገዙ