የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተሰሩ ሥራዎች ለውጦች መመዝገቡን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ገለጹ ።

  • Post last modified:April 25, 2025

ኃላፊው ይህን ያሉት የ2017 ዓ/ም 9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት በተደረገበት ወቅት ነው።

የ9 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የቀረበው ሁሉም የቢሮው ማኔጀመንት አባላትና ባለሙያዎች በተገኙበት ነው

የክልሉ ጤና ቢሮ አፈጻጸሙ በቀረበበት ወቅት ተግባርን እየከወነ ያለው ተቋም በዘላቂነት ለመፍጠር በሚያስችል መልክ ተግባራት እየተመሩ እዛው ሳለ በዋና ዋና ግቦች የሁሉን-አቀፍ የጤና ሽፋን እድገትን በማፋጠን፣ የሕብረተሰቡን ከድንገተኛ የጤና አደጋዎች መጠበቅ፣ አባ/እማወራ ትራንስፎርም ማድረግን እና የጤና ስርዓቱን ምላሽ ሰጪነትን መሻሻል እውን በማድረግ የሕብረተሰቡን የጤና ሁኔታ ማሻሻል እንደነበረ በሪፖርቱ ቀርቦዋል ፡፡

የ2017 የሴክተር ዕቅድ ዝግጅት በሚመለከት የ2017 በጀት ዓመት የክልሉ የጤና ዘርፍ እቅድ በዋናነት የ2016 አፈጻጸምን እና በሰባት ዓመቱ እቅድ ውስጥ ለ2017 ከተቀመጡ ግቦች ጋር በተናበበ መልኩ እንዲዘጋጅ በማድረግ ወደ ተግባር መገባቱን ተነስቶዋል ፡፡

በ9 ወራት በየደረጃው የሚታዩ የአመራር እና በባለሙያው ያሉ ክፍተቶችን እና ማነቆዎችን የመፍታት ስራ እንዲሁም ያሉ ጥንካሬዎችን የማስፋት ስራ ለመስራት ቁርጠኝነትና ተጠያቂነት ላይ ያተኮረ የውይይት ሠነድ በማዘጋጀት በየደረጃው በተለያየ ጊዜ የንቅናቄ መድረኮች ማካሄድ ተችሏል፡፡ በዚሁም መልካም የሚባሉ ውጤቶች ተመዝግቧል

ከህብረተሰቡ፣ከአጋሮች የህክምና ግብዓት ለሟሟላት እና የተለያዩ ግንባታ ለመፈጸም ሀብት የማሰባሰብ ስራ በ9 ወራት 400 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ልዩ ልዩ መድኃኒትና የህክምና ቁሳቁሶች አቅርቦት እና እንዲሁም ግንባታዎች ተከናውኗል ፡፡

በ2ኛ ግማሽ ዓመት ላይ የ2017 ክልላዊ የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ፌስቲቫልና የንቅናቄ መድረክ በማካሄድ ፕሮግራሙን የማነቃቃትና ወደ ተግባር የመመለስ ስራ ስኬታማ በሆነ መልኩ ተሰርቷል፡፡

የጽዱ ኢትዮጵያ ፕሮግራም በሁሉም በተመረጡ ወረዳዎች ከተማ እና በገጠር ተግባራዊ እየተደረገ ነው።

በአብዛኛዎቹ የጤና ተቋማት በየሩብ ዓመቱ የማህበረሰብና የባለሙያዎች ውይይቶች እና የባለሙያዎች ፎረም እየተካሄደ ይገኛል።

በ2017 በጀት ዓመት የአባ/እማ የማአጤመ የአባልነት ሽፋንን 80% መፈጸም ተችሏል፡፡

የማዐጤመ ሀብትን ከማሰብሰብ አንጻር በ2017 ዓ/ም በጀት ዓመት በጠቅላለ ከ651.5 ሚሊየን ብር በላይ ማሰብሰብ የተቻለ ሲሆን 93% ወደ ባንክ አካውንት መግባቱ ተረጋግጧል።

የተለያዩ ወረርሽኝ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች የተከሰተ ቢሆንም ቡዙ ጉዳት ሳያስከትል ለመቆጣጠር ተችሏል፡፡

በወባ በሽታ 408,054 ታማሚዎች ሪፖርት የተደረጉ ሲሆን ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አንፃር ሲነጻጸር በ76,705 (23%) ጨምሯል። በቀጣይ በልዩ ትኩረት ወባን የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራ በተገቢው በተቀናጀ መልክ እንዲሰራ አሳስበዋል

በ2017 በጀት ዓመት በመጀመሪያው 9 ወራት በ2,636 ጤና ተቋማት ላይ የቁጥጥር ስራ ለመስራት ታቅዶ በ2,636 (100%) ማከናወን ተችሏል፡፡

በጥቅሉ ከቅድመ ዝግጅት፣ በተግባር ምእራፍ እየሰራን ያለው ስራ በድጋፍና ክትትል እንደ ቢሮ በጋራ እና ፕሮግራም በለየ መልክ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በጉድለት ያሉት በቀሪ 3 ወራት ተግባሩን ይበልጥ ለማሳካት መስራት ከዚሁ ጎን ለጎን የተጀመረው 2018 እቅድ ዝግጅት ፈጥኖ እንዲጠናቀቅ በማድረግ መሰራት እንዳለባቸው ሁሉም በየደረጃዉ ያለው አመራር እና ባለሙያ ተቋም በሚፈጥር መልክ የተጀመሩ ስራዎች እንዲቀጥል በሚል ማጠቃለያ ሰጥተዋል።

በአብርሃም ሙጎሮ