በክልሉ የጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራ እና ተንተና ስራ አቅም መጠናከር በመረጃ ላይ የተመሰረተ የጤና ውሳኔዎችን ለማሳደግ ከፍተኛ እገዛ እንዳለው ተገለጸ ፡፡

  • Post last modified:May 19, 2025

የማዕከላዊ ኢትዮጽያ ክልል ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጤና መረጃ አስተዳደር ቅመራ እና ተንተና ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡በከቅም ግንባታ ስልጠናው ከክልሉ ጤና ቢሮ ፣ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ፣ ዩኒቨርሲቲ እና ኮሌጅ የተውጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል ፡፡ በስልጠና ማጠቃለያው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አቶ ማሙሽ ሁሴን የጤና ውሳኔዎች በበቂ መረጃ ላይ መመስረት የሚገባው በመሆኑ የመረጃ አስተዳደር ቅመራ እና ትንተና አቅም ማሳደግ ይገባል ብለዋል ፡፡ የጤና ስርዓትን ጥራት ባለው እና ተዓማኒ በሆነ የመረጃ ስርዓት ላይ እንዲዲከናወን በዘርፉ የሚስተዋለውን የባለሙያ አቅም እና ክህሎት ማዳበር ማስፈለጉን ገልጸዋል ፡፡ የመረጃ ተደራሽነትን ማሳደግ እንዲሁም ደህንነቱን ማረጋገጥ እንደሚገባም አቶ ማሙሽ አስታውቀዋል ፡፡ ተሳታፊዎች በስልጠናው ያገኙትን አቅም ወደ ተግባር በመቀየር በርካታ ውጤቶችን ማምጣት ይጠበቅባቹሃል ብለዋል ፡፡ በክልሉ ጤና ቢሮ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የጥናት ምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር ዶ/ር ስናፍቅሽ አየለ በበኩላቸው የጥናት እና ምርምር ስራዎችን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የዘርፉን ሽግግር ማጠናከር መሆኑን ገልጸው የዛሬው ስልጠና ጥናት እና ምርምሮች ላይ የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ ከጤና ቢሮ ከዩኒቨርሲቲ እና ኮሌጅ ለተውጣጡ ተሳታፊዎች ስልጠና መሰጠቱን ገለጸው በዘርፉ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲመጣ አጋዥ እንደሆነ ገልጸዋል ፡፡በኢንስቲትዩቱ የመረጃ አስተዳደር ትንተና እና ቅመራ ማዕከል ዳታ ማናጀር አቶ ሳሙኤል ሃይሉ በበኩላቸው ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ችግር ፈቺ ጥናት እና ምርምሮችን በመስራት በመረጃ ማዕከል ለውሳኔ ሰጪ አካላት በሚያግዝ መልኩ ለማደራጀራት ይሰራል ብለዋል ፡፡በቢኒያም ገዙ