በሀዲያ ዞን በጊምቢቹ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የተገነባው ሞዴል የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ተመረቀ ፡፡ ሰኔ 17/2017 ዓ.ም

  • Post last modified:June 25, 2025

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በጊምቢቹ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ከ 3.8 ሚሊዮን ብር በላይ ያስገነባውን ሞዴል የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት አስመረቀ ፡፡በምረቃው የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሐዬሶ፣ የሀድያ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ ዶ/ር ደሳለኝ ሽጉጤ፣ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት አባላት፣ የንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮምፕርሔንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ይድነቃቸው ደዳቸው፣ የጊምቢቹ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ታገሰ ተመስገን እና የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል።መድሀኒት ቤቱን ሰርቶ ለማጠናቀቅ ከ 2.8 ሚሊዮን ብር በላይ የፈጀ ሲሆን በተጨማሪም መድሀኒት ቤቱን ለማቋቋም ከ 1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የተለያዩ መድሀኒቶች በንግስት እሌኒ ሆስፒታል ድጋፍ የተደረጉ ሲሆን በጠቅላላው ከ 3.8 ሚሊዮን ብር የሚበልጥ ድጋፍ በዩኒቨርሲቲው ተደርጓል።በምርቃቱም ወቅት የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በእለቱ ጥሪ ከተደረገላቸው እንግዶች እና የስራ ሀላፊዎች ጋር በጋራ በመሆን ሆስፒታሉን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።የሀድያ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ሽጉጤ እንደገለጹት ዛሬ በጊምቢቹ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እንዳስመረቅነው ሞዴል የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት በጋራ ተባብረን ከሰራን በቀጣይም ሌሎች አካባቢዎም መስራት እና ማስመረቅ እንችላለን ብለዋል።የንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮምፕርሔንሲቭ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ይድነቃቸው ደዳቸው እንደገለጹት በመደበኛ መድሀኒት ቤት ይቀርብ የነበረው የመድሀኒት አቅርቦት በቂ ባለመሆኑ የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት ገንብቶ አገልግሎት ማስጀመሩ አስፈላጊ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይ የጊምቢቹ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ማኔጅመንት አባላት ዛሬ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ መርቆ ስራ ያስጀመረውን መድሀኒት ቤት አቅርቦት ዘላቂ እንዲሆን ማስቻል እንዳለባቸውም አሳስበዋል።የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሐዬሶ በመልዕክታቸው እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲዎች ካላቸው ተልዕኮዎች አንደኛው የማህበረሰብ አገልግሎት መሆኑን ጠቅሰው በዛሬው እለት ያስመረቅነው ሞዴል የማህበረሰብ መድሀኒት ቤት በሆስፒሉ ውስጥ እና ከሆስፒታሉ ውጭ ላሉ ታካሚዎች ትልቅ እፎይታን እንደሚፈጥር ጠቅሰው በቀጣይም መሰል ድጋፎች እንደሚቀጥሉም ተናግረዋል።ሰኔ 17/2017 ዓ.ምበዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ን/እ/መ/መ/ኮ/እ/ ሆስፒታል