የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ገባኤውን በማካሄድ ላይ ነው ፡፡

  • Post last modified:October 4, 2025

‘በባለቤትነት ላይ የተመሰረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ’ በሚል መሪ ቃል በቡታጅራ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል ።

ጉባኤውን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ በይፋ አስጀምረውታል ፡፡

በጉባኤው የመጀመሪያ ቀን ውሎ በክልሉ ጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታን እውን ለማድረግ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ውይይት የቡድን ውይይት ተካሂዷል ፡፡

ውይይቱን የቢሮ ምክትል ኃላፊዎች የማኔጅመንት አባላት የመሩት ሲሆን የዞን እና ልዩ ወረዳ ጤና ኃላፊዎች ፣ የወረዳ እና ከተማ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊዎች ፣ የሆስፒታል እና ጤና ጣቢያ ስራ አስኪያጆች ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ፣ ላብራቶሪ እና ደም ባንክ አመራሮች ፣ አጋር አካላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል ፡፡

በቡድን ውይይቱ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ሃሳቦች በቡድን አወያዮች ምላሽ የተሰጠ ሲሆን በሁለተኛ ቀን የጉባኤ ውሎ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ምላሽ ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ፡፡