
በመግባባት ላይ የተመሰረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የጤና ቢሮ ጉባኤ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የወረዳ እና ከተማ ጤና ጽ/ቤቶች እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ፡፡
ከወረዳዎች መካከል አንደኛ ሶዶ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ፣ ሁለተኛ ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ፣ እዣ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ወጥተዋል ፡፡
ከከተማ ጤና ጽ/ቤት መካከል አንደኛ ወልቂጤ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ፣ ሁለተኛ ቡታጅራ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ፣ እኩል ውጤት በማምጣት ሶስተኛ ደረጃ የወጡት ሆሳዕና እና ዱራሜ ከተማ ጤና ጽ/ቤቶች እውቅና እና ሽልማት በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴታ ሳህረላ አብዱላሂ ተበርክቶላቸዋል ፡፡