
(ታህሳስ 16/2018)
ሆስፒታሉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ መርቀውታል ፡፡
የክልሉ እና የፌደራል የስራ ኃላፊዎች የአንጋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን ተዘዋውረው ጉብኝት አድርገዋል ፡፡
በምረቃ መርሐ ግብር ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ፣ የከምባታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አረጋ እሸቱ እና ሌሎች ከፌደራል እና ከክልል የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

