
የ”BIG Catch up” የክትባት ዘመቻ አፈጻጸም ግምገማ በዛሬው ዕለት ከባለድርሻ አካላት ጋር በሆሳዕና ከተማ እያካሄደ መሆኑን የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ ገልጿል።
የቢሮው ምክትል ኃላፊና የጤና ፕሮግራሞች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ጴጥሮስ ክትባት ጀምረው ያቋረጡ እና ምንም ክትባት ያላገኙ ህጻናትን በዘመቻው ክትባት ቢሮው በትኩረት እየሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።
በሽታን የመከላከል እና የፈውስ ህክምና ተደራሽ የሚያደርገው የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን የጠቆሙት አቶ አሸናፊ ጥራቱ እና ደህንነቱ የተረጋገጠ ክትባት አገ/ት ተደራሽ ማድረግ የህጻናትን ህመምና ሞት በመቀነስ ረገድ ጉልህ ፋይዳ አለው ብለዋል ።
የክትባት አገ/ት እንደ ሀገር ከተጀመረ ረዥም ጊዜ ያስቆጠረ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ውጤት ሊያመጣ የሚችል የናሽናል ጋይድ ላይን በማዘጋጀት የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎች መነደፋቸውን ያመላከቱት ኃላፊው የ”BIG Catch up” የክትባት ዘመቻው በዋናነት የሚጠቀስ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
በሀገር ደረጃ 3.6 ሚሊዮን የሚጠጉ እድሜያቸው ከአምስት አመት በታች ያሉ ህጻናት ክትባት ጀምረው ያቋረጡ መሆኑን አቶ አሸናፊ አክለው ገልጸዋል።
በክልሉ ክትባት ያላገኙ 185 ሺህ ህጻናት እንደሚገኙ የጠቆሙት ምክትሉ አምስት ከተማ አስተዳደሮች እና 11 ወረዳዎች ላይ በ”BIG Catch up” የክትባት ዘመቻ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ እንደነበረ አውስተዋል።
የመድረኩ ዋና ዓላማ የ2016 በጀት ዓመት የ”BIG Catch up” የክትባት ዘመቻ አፈጻጸምን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑም ታውቋል።
የማ/ኢት/ክ/መ/ጤና ቢሮ