
ቢሮዉ” በጤና መረጃና ዲጂታል ፈጠራዎች ላይ ዘላቂ እንቨስትመንት በማድረግ የጤና ትሩፋቶችን እናሳድግ!” በሚል መሪ ቃል የመረጃ እና ዲጂታል ጤና ሳምንት ከሰኔ 8/2018 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት በተለያዩ ዝግጅቶች መከበር ጀምሯል ።
የጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት እንደ ክልል ዲጂታል ጤና እና የመረጃ ስርዓትን ከማጠናከር አንፃር ቢሮዉ ዉጤታማ ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
እንደ ሀገር በ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያን እዉን ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ የጠቆሙት ሀላፊዉ በክልሉ ሁሉ አቀፍ የጤና አገልግሎትን ዲጂታላይዝ በማድረግ ረገድ ሰፋፊ ተግባራት መከናወናቸውን አስረድተዋል ።
በክልሉ 12 ሆስፒታሎችን ከወረቀት ነፃ አገልግሎት መተግበራቸውን ያወሱት ሀላፊዉ በተሰሩ ስራዎች ሁሉም ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ እና ጠቅላላ ሆስፒታሎችን ከወረቀት ነጻ አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ መቻሉን ገልጸው አሁንም የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎችን ከወረቀት ነፃ በማድረግ የመረጃ ስርዓታችንን ዘላቂ በሆነ መልኩ እያሳካን እንገኛለን ብለዋል።
በክልሉ 10 ወረዳዎች ከወረቀት ነጻ አገልግሎት እንዲጀምሩ በተሰሩ ስራዎች ሶስት ወረዳዎች በመተግበር ላይ መሆናቸውን ጠቅሰዋል ፡፡
ተአማኒነት ያለዉን መረጃ በማደራጀት፣በመተንተን እና በተገቢው በመያዝ ጥቅም ላይ የማዋል ባህልን ማሳደግ እንደሚገባም አቶ ሳሙኤል አክለዋል።
የጤና መረጃ ስርዓታችን የአንድ ሳምንት ብቻ መሆን የለበትም ያሉት ሀላፊዉ ጥራት ያለዉ መረጃ የሁል ጊዜ ተግባሮቻችን ሊሆን እንደሚገባም አንስተዋል
የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ አቶ ሸምሱ ሀይረዲን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን ባስተላለፉበት ወቅት እንደገለፁት እንደ ዞን የጤና መረጃን በማጠናከር ረገድ በርካታ ዉጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል ።
የመረጃ ወቅታዊነትን በማጠናከር ትክክለኛ እና ወጥነት ያለዉ መረጃ ለዉሳኔ ሰጪነት በመጠቀም የጤና ስራዎችን ከምንጊዜዉም በላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል ።
በመድረኩ የጤና ቢሮ ምክትል ሀላፋዎች፣ የቢሮ የማነጅመንት አካላት፣ የዞንና የልዩ ወረዳ ጤና መምሪያ ሀላፊዎች፣አጋር አካላት እንዲሁም ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈዉ ብሔራዊ የጤና መረጃ ሳምንት የተለያዩ ሰነዶች ቀርበዉ ዉይይት እየተደረገባቸው ይገኛል ።
በሸምሲያ አደም

