
(ወራቤ ፣ሰኔ 11/2018) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ካውንስል የምግብ ስርዓት ሽግግር እና ኒውትሬሽንና የቀዳማይ የልጅነት ፍኖተ ካርታ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በሆሳዕና ከተማ እየተካሔደ ነው
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር )እንደገለጹት የምግብ ስርዓት ሽግግርና ፍኖተ ካርታ አብይ ዓላማ ያደገና ዘላቂ የምግብ ስርዓት መፍጠር ነው ብለዋል።
ከግብርና ትራንስፎርሜሽን ስራ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው ያመላከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ የግብርናው ዘርፍ ሲሻሻል የምናልማቸውን ግቦች ማሳደግ እንደሚያስችልም አስረድተዋል።
ህጻናት በልጅነታቸው በሚመገቡት፣በሚያዩት፣በሚሰሙት እና በሚዳስሱት ጉዳዮች ላይ ተጽዕኖ ያድርባቸዋል ብለዋል።
በሁሉም ዘርፍ ጤናማና ንቁ ዜጋ ለመፍጠር በህጻናት የልጅነት ዘመን ላይ በትኩረት መስራት ተገቢ ስለመሆኑም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
በትውልድ ግንባታ ላይ መስራት ለሀገር ግንባታ የሚኖረው አበርክቶ ከፍተኛ ነው ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ በንግግራቸው አመላክተዋል።
የኢትዮጵያ የቀዳማዊ የልጅነት ፕሮግራም ማናጀር ሰለሞን ተስፋዬ (ዶ/ር)በበኩላቸው የምንገኝበት ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታ ከአስተዳደጋችን ይመነጫል ብለዋል።
ለህጻናት ጫወታን መሰረት ያደረገ የማስተማር ስነ ዘዴን ማስፋት ተገቢ መሆኑን አብራርተዋል።
የመዝናኛ ፓርኮችን እና ሌሎች መሰል የመጫወቻ ስፍራዎችን ማመቻቸት ለትውልድ ግንበታ አስፈላጊ መሆኑን ዶ/ር ሰለሞን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ተወካይ አቶ ደበሌ ደበላ እንደገለጹት የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት ሽግግር እና ኒውትሬሽን በልዩ ልዩ ክልሎች ተግባራዊ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፕሮግራሙ ተጠቃሚ በመሆኑ ያሉትን ጸጋዎች መሰረት በማድረግ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርም አብራርተዋል።
የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት ሽግግር እና ኒውትሬሽን የያሉትን ፕሮግራሞች እና መንግስት የነደፋቸውን በፓይለት የምግብ ሉአላዊነት ለማስጠበቅ የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል።
ክልሉ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ባለቤት ነው ያሉት አቶ ደበሌ ይህም የኢትዮጵያን የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት የሚደግፍ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል።

