
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የልማት እቅድ ዳይሬክቶሬት የPMT አፈጻጸም በዘርፍና በየዳይሬክቶሬቶች ደረጃ የመረጃ አጠቃቀም ስርዓት ላይ ግምገማ አካሄደ።
የቢሮው የጤና ልማት ዕቅድ ክትትል ግምገማ እና ግብረመልስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አይሌ ለማ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ወቅታዊና ጥራቱን የጠበቀ መረጃን በመጠቀም በማስረጃ ላይ የተመሰረተ የዉሳኔ አሰጣጥን ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል
የመረጃ ባለቤትነት እና ተጠያቂነትን በማጎልበት ለዉሳኔ አሰጣጥ ስርዓት ግብዓት እንዲሆን መጠቀም ይገባል ያሉት ዳይሬክተሩ በክልሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመረጃ ጥራትን ለማሻሻል በሁሉም የጤና መዋቅሮች በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የጤና ልማት ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ተከታታይነት ያለው ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎችን ስለ መስራቱ ያወሱት አቶ አይሌ የጤና አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ ዕቅድ በየደረጃዉ ለሚገኙ የጤና ተቋማት መውረዱንም አስረድተዋል
በበጀት ዓመቱ በተገኙ ዉጤቶች ጠንካራ የአመራሩ ድጋፍ በመኖሩ እና ለጤና ዕቅድ ስኬት ቁርጠኝነት የታየበት ነዉ ያሉት አቶ አይሌ በቢሮው ውስጥ የሚገኙ ዳይሬክቶሬቶችም ዕቅዳቸውን በመረጃ በማስደገፍ ከመፈጸም አንጻር አበረታች ደረጃ ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
የቢሮውን የጤና አፈጻጸምን ለማሻሻል መረጃን መሰረት ያደረገ የተደራጀ ሪፓርት በየወሩ መላክ እንዳለበት የተናገሩት ዳይሬክተሩ በቀጣይም የመረጃ ጥራትን ይበልጥ ለማሻሻል እና ክፍተቶችን ለማረም የተጠናከረ ክትትል ይደረጋል ብለዋል።
በግምገማ መድረኩ ላይ በየዘርፉ እና በየዳይሬክቶሬቱ የተፈጸሙ ቁልፍ የጤና አፈጻጸሞች ቀርበው ግብረ መልስ ተሰጥቶባቸዋል ።
በሸምስያ አደም

