በበጀት ዓመቱ አስር ወራት በክልሉ የጤና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ውጤታማ ስራ መሰራቱን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ገለጹ፡፡

  • Post last modified:June 8, 2026

በቢሮው የጤና ሀብት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የ10 ወራት አፈፃፀም ተግባራት ግምገማ ተደርጓል፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በተገኙበት የጤና ኃብት ልማት እና አስተዳደር ዘርፍ የ2018 በጀት ዓመት የ10 ወር እቅድ አፈፃፀም ተግባራት ላይ እና በቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ዘሪያ ሰፊ ዉይይት ተደርጓል።

የጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት የህብረተሰቡን የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋፋት በርካታ የጤና ተቋማት ተገንብተው ለአገልግሎት ማብቃት መቻሉን ገልጸዋል ፡፡

ከክልል ጀምሮ በየደረጃው በሚገኙ መዋቅሮች የህብረተሰቡን የጤና ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የጤና ተቋማት ተገንብተው ግብዓት በማሟላት አገልግሎት ማስጀመር መቻሉን ጠቅሰዋል ፡፡

ውጤታማ ስራዎችን ለማጠናከር በቀጣይም ህጋዊ አሰራር የተከተለ ጠንካራ ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል ፡፡

በየደረጃው በሚገኙ የጤና ተቋማት ላይ የህብረተሰብ ተሳትፎ በማሳደግ አፈጻጸምን ብቻ ሳይሆን የአገልግሎት ጥራት ላይ ትኩረት በማድረግ የመጣዉን መሰረታዊ ዉጤቶች በቀሪ ወራትም ማስቀጠል እንደሚገባ አቶ ሳሙኤል አስረድተዋል።

የህብረተሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ አጋር አካላትን ማስተባበር እንደሚገባም ገልጸዋል ።

የማ/ኢ/ክ/ጤና ቢሮ ምክ/ሀላፊና የጤና ሀብት አስተዳደርና ፋይናንስ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሙሳ ኢዶሳ በበኩላቸዉ የ2018 በጀት ዓመት የ10 ወር አፈፃፀማችን ጥሩ ዉጤት የተመዘገበበት መሆኑን ጠቅሰዉ በቀጣይ ያሉ ክፍተቶችን በመፍታት የተሻለ ለመፈጸም ጥረት እንደሚደረግ ገልጸዋል ፡፡