የመረጃ እና የዲጂታል ስርዓት ለማሻሻል የሚያግዙ 185 ኮምፒተሮችን በክልሉ ለሚገኙ ሆስፒታሎች ድጋፍ ተደረገ ፡፡

  • Post last modified:June 29, 2026

የክልሉ ጤና ቢሮ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የሆስፒታሎች የዲጂታል መረጃ አያያዝን ስርዓትን የሚያሻሽሉ ዘርፍ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን ተገልጿል ፡፡

ቢሮው ከጤና ሚኒስቴር ያገኘውን የኮምፒተር ድጋፍ በክልሉ ለሚገኙ የስራ ሆስፒታሎች የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል እና የመረጃ አያያዝን ዘመናዊ ለማድረግ ድጋፍ አድርጓል።

በርክብክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የህክምና አገልግሎቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብቴ ገ/ሚካኤል እንደገለጹት፤ ይህ ድጋፍ በጤና ተቋማት የሚሰጠውን አገልግሎት ፣ ቀልጣፋ እና ወቅቱን የጠበቀ ለማድረግ፣ የመረጃ አያያዝና አሰጣጥ ስርዓቱን የተሳለጠ ለማድረግ፣ የተገልጋዮችን እንግልት በመቀነስ የአገልግሎት ጥራትን ለማሳደግ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡

የጤና ተቋማትን አገልግሎት ከወረቀት ነጻ /paperless/ ለማድረግና ጥራትን ለማሻሻል እንደሚያግዝ አቶ ሀብቴ ገ/ሚካኤል አስታውቀዋል ፡፡

የኮምፒውተር ድጋፉ ተቋማቱ ከወረቀት ነጻ ወደሆነ አሰራር እንዲሸጋገሩና የመረጃ ስራቸውን እንዲያሳልጡ ታስቦ የተደረገ በመሆኑ፣ ኮምፒውተሮቹ ኮምፒውተሮቹ ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ እንዲውሉ አደራ ብለዋል።

በርክክቡ የጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሞሳ ኢዶሳ ተገኝተዋል ፡፡

ዝናሽ ደለለኝ