የተሻሻለው የጤና ኤክስቴንሽን ፍኖተ ካርታ በመተግበራችን የበሽታ መከላከል ስራችን አክሞ የማዳን አቅማችን እንዲሻሻል አድርጓል አቶ ሳሙኤል ዳርጌ

  • Post last modified:July 4, 2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ የዋሽ እና አካባቢ ጤና የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ መድረክ መካሄድ ጀመረ ፡፡

በበጀት ዓመቱ በሽታ መከላከልን ታሳቢ ያደረገ የዋሽ እና አካባቢ ጤና ፕሮግራማችን ባለ ድርሻ አካላትን በማስተባበር በተሻለ መፈጸም መቻሉን የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በመድረኩ መክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል ፡፡

ጽዱ ኢትዮጽያ ስንተገብር ከውስጥ ወደ ውጪ መሆን እንዳለበት የጠቀሱት አቶ ሳሙኤል በክልሉ ጽዱ ወረዳ ፣ ጹዱ ጤና ፣ የሀይማኖት እና የትምህርት ተቋማት ለመፍተጠር እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል ፡፡

የጽዱ ኢትዮጽያ ፕሮግራም በክልሉ በፓይለት ደረጃ 2016 በ3 ወረዳዎች ተጀምሮ በ2017 በጀት ዓመት በ7 ወረዳዎች ተጨምረው አሁን አስር ወረዳዎች መድረሱን ጠቅሰው ሁለት ወረዳዎች ጽዱ ማድረግ መቻሉን አቶ ሳሙኤል ጠቅሰዋል ፡፡

በሽታን ለመከላከል የቤተሰብ ሳኒቴሽን ሽፋን ማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን ገልጸው አማራጭ የንጽህና ግብዓት በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርቡ በ71 ማህበራት ድጋፍ መደረጉንም አስታውቀዋል ፡፡

ተቋማት ጽዱ እንዲሆኑ
ጽዱ ጤና ተቋም መፍጠር ላይ በተሰራው ስራም 57 ጤና ተቋማት ከዋሽ እና ኮ ዋሽ ትብብር ጽዱ ጤና ተቋም ፕሮግራም እየተተገበረ መሆኑን አስስተው ጽዱ ትምህርት ቤት ጽዱ የእምነት ተቋማት የመፍጠር ስራዎች ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል ፡፡

ከክልሉ ቴክኒክ እና ሙያ ቢሮ ጋር በመተባበር 20 ዘመናዊ ሞዴል የመንገር ዳር ሽንት ቤቶች መገንባታውንም ጠቅሰዋል ፡፡

የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አየለ ፈቀደ በበጀት ዓመቱ በዋሽ እና አካባቢ ጤና ላይ ንቅናቄ በመፍጠር በተሰራው ስራ በዋሽ እና አካባቢ ጤና
የጎዳና ላይ መጸዳጃ ቤቶችን የመገንባትን ጨምሮ ጽዱ ወረዳ ፕሮግራም እየተገበረ መሆኑን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው ጠቅሰዋል ፡፡